በሰላም እና በደስታ ሁሉ ተሞሉ

በሰላም እና በደስታ ሁሉ ተሞሉ

የተስፋ አምላክም በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በተስፋ እንድትበዙ በማመናችሁ ደስታንና ሰላምን ሁሉ ይሙላባችሁ፡፡ – ሮሜ 15፡13

ከብዙ ዓመታት በፊት በህይወቴ ምንም ደስታና ሰላም ፈፅሞ በሌለበት ሰአት በከባድ ሁኔታ ውሰጥ አልፊያለሁ፡፡ በእያንዳንዱ ጊዜ ስህተት ስሰራ፣ ራሴን ‹ፍፁም ክርስቲያን› መሆን እንደማልችል በመቁጠር በፍጥነት ራሴን እወቅሰዋለሁ፣ በራሴም እናደዳለሁ፡፡

አንድ ቀን ታዲያ፣ በአጋጣሚ ሮሜን 15፡13 ላይ ‹‹የተስፋ አምላክም በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በተስፋ እንድትበዙ በማመናችሁ ደስታንና ሰላምን ሁሉ ይሙላባችሁ፡፡›› የሚለውን እውነት አገኘሁት፡፡

ወደጥርጣሬና ወደአለማመን ዘው ብዬ በችኮላ እንደገባሁ እና ለሰይጣንም አዕምሮዬን በቁጣ፣ በክፋት እና በአሉታዊነት እንዲያጠቃኝ እንደፈቀድኩለት ተረዳሁ፡፡ በሂደትም እግዚአብሔርን መታመንና ቃሉን ማመን ምን ያህል ሰላምንና ተስፋን እንደሚያመጣና ድካሜን ለማሸነፍ እንደሚረዳኝ እረስቼው ነበር፡፡

የእግዚአብሔር ቃል መልሱን ሰጥቶኛል፡፡ ኢየሱስ የወደደኝ፣ ያለፈው ሃጢአቴን ይቅር ሊለኝ ብቻ ሳይሆን፣ ወደፊት ለሚኖሩት ድካሞቼ ሁሉ ጭምር ነው፡፡ ስለዚህ ሰይጣን ጥያቄዎችናና አለማመንን ውስጤ ቀስ በቀስ እንዲያስገባ አልፈቅድለትም ፣ እናንተም መፍቀድ የለባችሁም፡፡

ሰላም፣ ተስፋና ደስታ በፊትለፊታችሁ እንዳሉ ዛሬ እወቁ፡፡ ወደ እግዚአብሔር ቃል ሂዱ፣ እምነታችሁንም ከፍ አድርጋችሁ አንቀሳቅሱት፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

ጌታ ሆይ! በየጊዜው የጠላትን ውሸት ማመን ስጀምር በቃልህ ውስጥ ያለውን እውነት አስታውሰኝ፡፡ አንተን በማመን፣ ዛሬ ሰላምንና ደስታን አገኛለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon