በቀል የእግዚአብሔር ነው

በቀል የእግዚአብሔር ነው

ወዳጆቼ ሆይ ለእግዚአብሔር ቁጣ ፈንታ ስጡ እንጂ አትበቀሉ፤ “በቀል የእኔ ነው፤እኔ ብድራትን እመልሳለሁ” ይላል ጌታ ተብሎ ተጽፏልና፡፡ -ሮሜ 12፡19

የሆነ ሰው ሲያናድደን ሰይጣን አናዶ ሊያቆየን ይፈልጋል፡፡ ጠላት እንድታደርጉ የማይፈልገው ተቃራኒ ነገር በምህረት እና በይቅርታ መመለስ ነው፡፡ምክንያቱም እናንተን አናዶ የማቆየት እቅዱን ያሸንፍበታል፡፡ በተፈጥሮ አይመጣም እናም ሁልጊዜ ቀላል አይደለም ነገር ግን የምንችለውን ስናደርግ እግዚአብሔር ደግሞ እኛ የማንችለውን ያደርጋል፡፡

አንድ ሰው ሲያናድደን እና ሲያስቀይመን የብዙዎቻችን ተፈጥሯዊ ምላሽ መልሶ ማናደድ ነው፡፡ ነገር ግን ከመለስንላቸው ምንድንው የምናተርፈው? የበለጠ እነርሱን ከማናደድ እና መልሰው እናንተን እንዲያናድዷችሁ ከማድረግ በቀር ፡፡ዙሩ መቼም አያልቅም!

ከንዴት ጋር ከተቆራኘን ሞኝ እየሆንን ነው ማለት ነው፡፡ንዴታችንን እና ያናደዱንን ሰዎች ለእግዚአብሔር አሳልፈን መስጠት እና እርሱ እንዲይዘው ማድረግ አለብን…በቀል የእኔ ነው፣እኔ ብድራትን እመልሳለሁ ይላል እግዚአብሔር፡፡

በእግዚአብሔር ታመኑ እርሱም ይጠብቃችኋል፡፡ የተፈጠረውን መቀየር አትችሉም ነገር ግን ለእግዚአብሔር አሳልፋችሁ ስትሰጡት በህይወታችሁ አንድን መልካም ነገር ለማድረግ ይጠቀምበታል፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ በቀል የአንተ ነው ብዬ አምናለሁ ለሰዎች በቁጣ መመለስ እኔ እንዳደርገው የምትፈልገው ነገር እንዳልሆነ ተረድቻለሁ፡፡ንዴቴን ለአንተ እሰጣለሁ እናም አንተ እንደምትጠነቀቅልኝ አምናለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon