በቃሉ ውስጥ የምትፈልገውን ኃይልና መልስ አግኝ

በቃሉ ውስጥ የምትፈልገውን ኃይልና መልስ አግኝ

የእግዚአብሔር ቃል ሕያውና የሚሠራ ነውና፤ በሁለት በኩል ስለት ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ ስለታም ነው፤ ነፍስንና መንፈስን፣ ጅማትንና ቅልጥምን እስኪለያይ ድረስ ዘልቆ ይወጋል፤ የልብንም ሐሳብና ምኞት ይመረምራል። – ዕብ 4፡12

ሰዎች መፅሃፍ ቅዱስን ከየት ጀምረው ማንበብ እንዳለባቸው ሲጠይቁኝ ከየትኛውም ቦታ ጀምረው ቢያነቡት ችግር አለመኖሩን እነግራቸዋለሁ፡፡ ሊያግዛችሁ የሚችል ማንኛውንም ነገር ማጥናት ትችላላችሁ።

እኔ መፅሃፍ ቅዱሴን ማንበብ ስጀምር ጥሩ ግንኙነት አልነበረኝም ምክንያቱም ፍቅር የሚባለውን ነገር በተገቢው አልተረዳሁም ነበር፡፡ ስለዚህ ስለፍቅር ምንነት ከሚያወራው ቦታ ማንበብ ጀመርኩኝ ፤ ፍቅር ማለት ከስሜት አልፎ ሰዎችን እንዴት አድርጋችሁ መንከባከብ እንዳለበችሁ የምትወስኑት ውሳኔ ነው፡፡

መፅሃፍ ቅዱስ ስለ ፍቅር የሚያስተምረውን በማጥናት የፍቅር ምንነት ገባኝ፡፡ ከዚያም ህይወቴ መቀየር ጀመረ፡፡

ምንም አይነት ነገር እያሳለፋችሁ ቢሆን ማውጫ ተጠቅማችሁ ጥቅስ ልታገኙለት ትችላላችሁ፡፡ ለምሳሌ ሰለፍርሃት፤ወይም ቁጣ ማንበብ ከፈለጋችሁ የመፅሃፍቅዱሳችሁ የመጨረሻ ገፅ ላይ ባለው ማውጫ ላይ ሄዳችሁ በመምረጥ ማንበብ መጀመር ትችላላችሁ፡፡ መንፈስ ቅዱስም እውነቱን እንዲገልጥላችሁና እንዲያሳያችሁ ጠይቁት፡፡

ማንኛውም ቦታ ላይ ማንበብ ብትጀምሩ ማስታወስ ያለባችሁ ነገር ቃሉ ሕያው እንደሆነ እና እግዚያብሔር ለልባችሁ ሊናገራችሁ እንደሚፈልግ ነው፡፡


ጸሎት ማስጀመሪያ

እግዚያብሔር ሆይ ልትናገረኝ እንደምትፈለግ አውቃለሁ በቃልህ ውስጥ ያለውን ኃይል እና ጥበብ ዛሬ እንዳገኝ እርዳኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon