በእርሱ ፍቅር ታማኝ ሁን

ስለዚህም እግዚአብሔር ለእኛ ያለዉን ፍቅር እናዉቃለን፤ በፍቅሩም እናምናለን፡፡ እግዚአብሔር ፍቅር ነዉ፤ በፍቅር የሚኖር በእግዚአብሔር ይኖራል፤ እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል፡፡ – 1 ዮሐ 4:16

1 ኛ ዮሐ 4፥16 ትኩረት የሚሰጠዉ እግዚአብሔር ለእኛ ያለዉን ፍቅር ልብ እንድንል ነዉ፡፡ ምን እያልን እንደሆነ ሳንረዳ እንኳ “እግዚአብሔር ይወደኛል” ማለት ለእኛ ቀላል ነዉ፡፡ ስለ እርሱ ፍቅር ያለን እዉቀት በአእምሮአችን የምንረዳዉ አንዳች መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሐቅ ብቻ ሳይሆን በሕይወታችን ያለ ህያዉ እዉነታ መሆን አለበት፡፡

ይህ ጥቅስ የሚለዉ እግዚአብሔር ፍቅር ነዉ፤ በፍቅር የሚኖር በእግዚአብሔር ይኖራል፤ እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል ነዉ፡፡

በዚህ ጥቅስ ‘የሚኖር’ የሚለዉ ቃል ‘ተማኝ መሆን፣ በፍቅሩ መኖር’ ማለቱ ነዉ፡፡ የሚጠቅሰዉም መጎብኘትን ሳይሆን መቆየትን ወይም እዚያዉ መሰንበትን ነዉ፡፡

የእግዚአብሔር ፍቅር የምንሸመድደዉ ሐቅ ወይም ብልጭ የሚል ስሜት አይደለም፡፡ የእርሱ ፍቅር እንዲህ ማለት ነዉ በመልካም ጊዜ የሚቆይና ነገሮች ሲከፉ የሚጠፋ ሳይሆን ሁሌ ነዋሪ ስለሆነ እኛም በፍቅሩ ልንጸና ይገባናል፡፡

እያንዳንዳችን ከበሰለ ክርስተና ነዶ መሰብሰብ የምንችለዉ በእግዚአብሔር ፍቅር ስንጨመቅ ነዉ፡፡ በአስደናቂዉ የእግዚአብሔር ፍቅር በታማኝነት ስንቆይ በአስቸጋሪ ጊዜያት እንኳ እናድጋለን፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

ጌታ ሆይ! ዛሬ አንተ ለእኔ ላለህ ፍቅር ታማኝ እሆናለሁ፡፡ ብዙ ነገሮች ይቀያየራሉ ግና የአንተ ፍቅር አይሄድም ስለዚህ በአስደናቂዉ ፍቅር ሥራ መስደድን መርጬአለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon