በእግዚአብሔር ሀሳብ፣ ፈቃድና ስሜት ዉስጥ መኖር

በእግዚአብሔር ሀሳብ፣ ፈቃድና ስሜት ዉስጥ መኖር

ብልቶቻችሁን የክፋት መሣሪያ አድርጋችሁ ለኀጢአት አታቅርቡ፤ ይልቁንስ ከሞት ወደ ህይወት እንደተሻገሩ ሰዎች አድርጋችሁ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር አቅርቡ፤ ብልቶቻችሁንም የጽድቅ መሳሪያ አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር አቅርቡ፡፡ – ሮሜ 6:13

ግዚአብሔር እያንዳንዳችንን የፈጠረን ከመንፈስ፣ ከነፍስና ሥጋ ነዉ፡፡ እንደ አማኞች ነፍስ አእምሮአችንን ፈቃዳችንንና ስሜታችንን እንደያዘች ልንረዳ ያስፈልጋል፡፡ በ“እኔ” እስከተሞላና ለመንፈስ ቅዱስ ለመገዛት ካልፈቀደ የግድ ሊጻዳ ይገባዋል፡፡

ነጻ ፈቃድ ስላለን የገዛ አእምሮአችን ምን እንድናስብ ይነግረናል ነገር ግን ሀሳባችን የእግዚአብሔር ሀሳብ ላይሆን ይችላል፡፡

እርሱ ለእኛ ከሚፈልገዉ ጋር ቢጋጭ እናኳ ፈቃዳችን የሚናገረዉ እኛ የምንፈልገዉን ነዉ፡፡

ምን እንዲሰማን የሚወስነዉ ስሜታችን ነዉ፡፡  ነገር ግን በክርስቶስ ልባችን ለእግዚአብሔር እና ለቃሉ ብቻ መገዛት አለበት፡፡

እግዚአብሔር የራሳችንን ሀሳብ ፈቃድና ስሜት በእርሱ እንድንተካ ይፈልጋል፡፡ እንደዛ እስካላደረግን ድረስ በሃጥያት ላይ ድል አድርገን መኖር አንችልም፡፡

ለእግዚአብሔር በነፍስህ የእርሱን መንገድ መከተል እንደምትፈልግ መንገር ጀምር፡፡ በሮሜ 6 ጳዉሎስ ራሳችንን ለእግዚአብሔር እንድናቀርብ አጥብቆ ያስገነዝበናል፡፡ ዛሬ ነፍስህን ለራስህ ለመጠቀም ሳይሆን ሁለንተናህን ለእግዚአብሔር ልታቀርብ ምረጥ፡፡

ነፍስ ስትነጻ የእግዚአብሔርን ሀሳብና ፍላጎት ለመሸከም ትሰለጥናለች፡፡ እናም ከዚያ በኋላ የእግዚአብሔርን ክብር የሚገለጥበት ሐይለኛ ሰዉ ትሆናለህ፡፡


የጸሎት ማስጀመሪያ

ጌታ ሆይ! አንዳንድ ጊዜ አእምሮዬ፣ ፈቃዴና ስሜቴ የአንተን ቃል ይቀረናል ነገር ግን በዚህ ህይወት መቀጠል አልፈልግም፡፡ አባት ሆይ አንተ እንደምታነጻትና እኔንም ፈቃድህን ለመፈጸም እንደምትጠቀመኝ አዉቄ ነፍሴን ለአንተ አስገዛለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon