በእግዚአብሔር ፊት እረፍ

ዕረፉ፥ እኔም አምላክ እንደ ሆንሁ እወቁ በአሕዛብ ዘንድ ከፍ ከፍ እላለሁ፥ በምድርም ላይ ከፍ ከፍ እላለሁ።መዝ 46:10

ንዱ ከዛሬዉ ዓለማችን መማር ምንችለዉ አስፈላጊ ነገር እንዴት የተረጋጋን መሆን እንዳለብን ነዉ፡፡

በእኔ እምነት ብዙዎቻችን እንድንቃጠልና እንድንጨነቅ ያደረገን አስፈላጊዉ ምክንያት እንዴት የተረጋጋን መሆን እንዳለብን ስለማናዉቅ ነዉ፡፡ እርሱን ለማወቅ በምናጠፋዉ ጊዜ ዝምታዉን ማድመጥ እንማራለን መንገዳችንን ሊመራ የሚችልበትን ትንሹን እና የተረጋጋውን ድምጹን እንሰማለን፡፡

የጌታን ድምጽ ሁል ጊዜ ለማድመጥ በሰላማዊ ሁኔታ ዉስጥ ማረፍን መማር ያስፈልገናል፡፡  ዛሬ ብዙ ሰዎች ከአንዱ ነገር ወደ ሌላኛዉ ይሮጣሉ፡፡ ምክንያቱን አእምሮአቸዉ መረጋጋትን አያዉቅም ልባቸዉም እንዴት መረጋጋትን እንዳለባቸዉ አያዉቅም፡፡

ብናርፍና የመንፈስ ቅዱስን ድምጽ ለመስማት አእምሮአችንን በጸጥታ ዉስጥ ብናደርግ ሰላማዊ ኑሮ እንኖራለን ለመታዘዝም ዝግጁ እንሆናለን፡፡ በእግዚአብሔር ፊት እስከቆየን ደረስ ከሁከት የጸዳ ሰላማዊ ህይወት መምራት ቀላል መሆኑን ማየት እንችላለን፡፡

የጸሎት መጀመሪያ

ጌታ ሆይ! አንተ ብቻ አምላክ እንደሆንክ እቀበላለሁ፤ በፊትህ ማረፍ ጠቃሚ እንደሆነ አዉቃለሁና በዉስጤ ሰላም ሆኜ ዘወትር ድምጽህን ለመስማት ዝግጁ እንድሆን እንዴት በፊትህ እንዳርፍ ምራኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon