በዓለም ነን እንጂ የዓለም አይደለንም

በዓለም ነን እንጂ የዓለም አይደለንም

‹‹…እኔ ቃልህን ሰጥቻቸዋለሁ፤ እኔም ከዓለም እንዳይደለሁ ከዓለም አይደሉምና ዓለም ጠላቸው›› (ዮሐ.17፡14) ።

የዛሬው የመጽሐፍ ቅዱሰ ክፍላችን የሚያስተምረን እንደ አማኞች እኛ በዓለም ውስጥ እንኖራለን፤ ነገር ግን እኛ ከዓለም አይደለንም፡፡ ይህም እኛ በዓለማዊ ንጽረተ ዓለም አመለካከት ወስደን ልንጠቀምበት አንችልም ማለት ነው፡፡ በህይወት አኗኗረር መንገዳችንና አመለካከታችን እንደዓለማዊ እንደሆን (ዓለምን በመምሰል) በቋሚነት መንቃት ያስፈልናል፡፡ ለመዝናኛ እንዲሆን ብለን በዓመጽ የተሞሉ ፊልሞችን መመልከት ይህ በዓለም እየሆነ እንዳለው ይህ ህሊናችንን የሚያደነዝዝና የሚያደነድን ሆኖ የእግዚአብሔርን ድምጽ እንዳንሰማ ዝግጁ (የነቃን) እንዳንሆን (የጎደልን) ያደርገናል፡፡ ዛሬ በዓለም ውስጥ ያሉ ብዙ ሰዎች ለሰዎች ስቃይና መከራ የማያዝኑ (የማይሰማቸው) ችልተኞች ናቸው፡፡ ምክንያም በቴሌቪዥን መስኮት የሚመለከቱት አሳዛኝ ምስሎች ስለሆነ ነው፡፡

የዜና አውታሮች ብዙውን ጊዜ (አብዛኘውን ጊዜ) ስሜት አልባ በሆነ ሁኔታ ሆነው የሚያስተላልፉት እጅግ አሳዛኝ ዘገባዎችን ነው፡፡ እኛ እነዚህን ዓይነት ጉዳዮች ያለምንም የሚገደው ስሜት እንመለከታቸዋለን፤ እንሰማቸዋለንም፡፡ ብዙ እጅግ ዘግናኝ ነገሮችን እየሰመን ያለምንም ዓይነት የርህራሄ ስሜት ላለው አሳዛኝ ነገሮች ተመጣጣኝ ምላሽ አንሰጥም ወይም ለሚታየው ዓመጻ መመለስ የሚገባንን አናደርግም፡፡

እነዚህ ሁሉ ነገሮች ሰይጣን በዓለም ላይ ያለው አጠቃላይ የራሱ እቅድ ክፍል ነው፡፡ እርሱ በዙሪያችን ለሚሆነው አስጨናቂ ክስተት ሁሉ ንቁ ሆነን እንዳንገኝ ልበ ደንዳና እና በስሜታችን የማይገደን እንድንሆን ይፈልጋል፡፡ በዙሪያችን ባሉ ሁኔታዎች ሰዎች ሲጎዱ የሚያገባን ሆነን እንድንገኝ አይፈልግም፡፡ነገረር ግን እንደ ክርስቲያን የሚሰማን፣ የሚያገባንና የምጸልይ መሆን ይጠበቅብናል፡፡ በማኛቸውም ጊዜ በዓለም ውስጥ በሚሆኑ ጉዳዮች ስንሰማ እርሱ ምን እንደሚስብ ወደ እግዚአብሔር መጸለይና እርሱ ለተከሰተው ክስተት የሚሰጠውን ምላሽ መርምሮ ማግኘት ይጠበቅብናል፡፡ ከዚያም እኛ የእርሱን ምላሽ መስማትና እንደሚያዘን እርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል፡፡ ይህ በዓለም ውስጥ መኖር የመቻላችን አንዱ መንገድ ነው ነገር ግ እኛ የዓለም አይደለንም፡፡

ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡ ለመንፈሳዊ እሴቶች አቋም ይኑርህ እንጂ አታመቻምች፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon