በየዕለት ተዕለት ህይወታችሁ ህልውናውን እንዴት መለማመድ ትችላላችሁ

በየዕለት ተዕለት ህይወታችሁ ህልውናውን እንዴት መለማመድ ትችላላችሁ

ኢየሱስም እንዲህ አለው፤“የሚወደኝ ቢኖር ቃሌን ይጠብቃል፤አባቴም ይወደዋል፤ወደ እርሱ እንመጣለን፤ከእርሱም ጋር እንኖራለን፡፡” – ዮሐ 14፡23

ህይወት በስራብዛት እና በእንቅፋት የተሞላ ነው፡፡በሚያስፈልጉን ነገሮች፣በኃላፊነቶቻችን እና በጭንቀቶቻችን በጣም በቀላሉ ከመያዛችን የተነሳ እጅግ በጣም የሚያስፈልገን ነገር ላይ ሳናተኩር እንቀራለን፡፡

በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ ሁለት መጨረሻ ላይ ዮሴፍ እና ማርያም ኢየሱስን በ አስራሁለት አመቱ ለፋሲካ በዐል ወደ ኢየሩሳሌም ሲወስዱት የሚተርክ አንድ የሚያስገርም አጭር ታሪክ ይገኛል፡፡ክብረ-በዐሉ ካለቀ በኋላ እሱም ከእነርሱ ጋር ያለ መስሏቸው ወደ ቤታቸው ለመመለስ ጉዞ ጀመሩ፡፡

ስንት ጊዜ ይሆን እግዚአብሔር ከእኛ ጋር እንዳለ ቆጥረን የራሳችንን ነገር ለማድረግ ከመስመር የወጣነው?

በጣም ደስ የሚለው ነገር ይሄ ነው፡፡ኢየሱስ ከእነርሱ ጋር እንዳልሆነ ከማወቃቸው በፊት ማሪያም እና ዮሴፍ የአንድ ቀን መንገድ ተጉዘው ነበር፡፡እናም እሱን መልሶ ለማግኘት ሶስት ቀን ፈጀባቸው፡፡ ሶስት ቀን! እዚህ ጋር ያለው መለክት ልዩ የሆነውን የእግዚአብሔር ህልውና ለማጣት መልሶ ከማግኘት ይልቅ ቀላል እንደሆነ ነው፡፡

በእግዚአብሔር ህልውና ውስጥ ለመቆየት ጠንቃቃ መሆን ይገባናል፡፡እንደዚህ ስናደርግ፣እግዚአብሔር በልባችን ውስጥ ቤተኝነት እንዲሰማው እናደርገዋለን፡፡

ይሄ በቀላሉ የሚጀምረው ለቃሉ ታዛዥ በመሆን ነው፡፡የመንፈሳዊ ብስለት ቅጥር አንድ መገለጫው እግዚአብሔር የማይወደውን ባህሪ ለመተው የሚደረግ ቁርጠኝነት ነው፡፡እሱ የሚያስበው ነገር ግድ እንደሚላችሁ የሚያሳይ ነው፡፡

ይሄም ማለት ለሌሎች ደግ ለመሆን መርጣችኋል፣ይቅርታ ማድረግን ተምራችኋል፣የተበደላችሁትን ትታችሁ በሰላም መኖር ችላችኋል ማለት ነው፡፡ቃላቶቻችንን አስበን ለመጠቀም ስንመርጥ፣እግዚአብሔርን ስናመሰግን እና ሌሎችን ስንረዳ ቀናችንን በሙሉ ከእግዚአብሔር ጋር እንደተያያዝን ይሰማናል፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

አባት ሆይ ልቤን ቤትህ ስላደረግከው አመሰግናለሁ፡፡ጌታ ሆይ ዛሬ ህልውናህን እፈልገዋለሁ፡፡በሃሳቤ እና በቃላቴ እንዳከብርህ እና በዙሪያዬ ላሉት በረከት እንድሆን እርዳኝ፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon