በድፍረት ወደ ዙፋኑ ቅረብ

በድፍረት ወደ ዙፋኑ ቅረብ

እንግዲህ ምሕረትን እንድንቀበልና በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ፣ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት እንቅረብ። – ዕብራዊያን 4፡16

እግዚአብሔር ወደ ጸጋው (ልዕለ ተፈጥሯዊ የሆነ የውስጥ ብርታት) መሮጥ ልማዳችን እንዲሆን ይፈልጋል፡፡ በእርሱ ብቻ እድንደገፍ ፍላጎቱ ነው፡፡ ሰይጣን በርካታ ስህተት በመፈጸማችን እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ጉዳይ እንደሌለው ፤ የማንጠቅምና በእግዚአብሔር ሕልውና ውስጥ ለመገኘት የማንመጥን እንደሆንን ይነገርናል ይሁን እንጂ ሰይጣን ውሸታም ነው፡፡

የእግዚአብሔር ቃል ግን እንደዛ አይደለም ሚለው፡፡ ቃሉ የሚለው ይቅር የተባልን ልጆች በመሆናችሁ በድፍረት ወደ ዙፋኑ መቅረብ ትችላላችሁ ነው ፤ ዛሬ በዚህ እውነት ለመኖር ምረጡ፡፡

‹‹እግዚአብሔር የሚወደኝ አይመስለኝም›› ፣ ‹‹ይቅር የተባልኩ አይመስለኝም›› ወይም ‹‹ እንደው የወደፌቴ ምን ይሆን›› አትበሉ ፤ መናገር ያለባችሁ እግዚአብሔር ይወደኛል ፤ ከእርሱም ፍቅር ማንም አይለኝም፡፡ ይቅር ስለተባልኩ አሁን ወደ እርሱ መቅረብ እችላለሁ ፤ እርሱ እኔን ስለተቀበለኝ ድፍረት አለኝ፡፡

አልረባም የሚል ስሜት በውስጣችሁ ሲነሳ የእግዚአብሔር ቃል አስታውሱ በድፍረትም ወደ ሰማይ አባታችሁ ሂዱ እርሱም እናንተን ለመቀበል ይጓጓል፡፡


ጸሎት ማስጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ በድፍረት ወደ አንተ እመጣለሁ ፤ ቃልህ ይቅር እንደተባልኩ እና ዘወትር ወደ አንተ መምጣት እንደምችል ይናገራል፡፡ ስለይቅርታህና ጸጋህ አመሰግንሃለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon