ስለምትሰሙት ነገር ጥንቃቄ አድርጉ፤ በምትሰፍሩበት መስፈሪያ ይሰፈርላችኋል፤ እንዲያውም ከዚያ የበለጠ ይጨመርላችኋል። ላለው ይጨመርለታል፤ ከሌለው ላይ ግን፣ ያው ያለው እንኳ ይወሰ ድበታል። (ማርቆስ 4:24)
በመጨረሻው ዘመን ብዙ ሐሰተኞች ነቢያት እንደሚነሱ እና የሚያሳክክ ጆሮዎቻቸው መስማት የሚፈልጉትን ለሰዎች እንደሚናገሩ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። ሰዎች የሚያስደስት እና የሚያዝናና ነገር የሚነግራቸውን ሰው ይፈልጋሉ። ምኞቶቻቸውን ለማሟላት እውነቱን ከመስማት ወደ ኋላ ይመለሳሉ ደግሞም ተረቶችን እና ሰው ሠራሽ ልብ ወለድ ወሬዎችን ለመስማት ይቅበዘበዛሉ (2 ጢሞቴዎስ 4:፡3– 4ን ተመልከት)።
“መንፈሳዊ” ተብለው ወደተሰየሙ ነገር በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ ድርሻ የሌላቸው መንገዶች ይመለሳሉ። “መንፈሳዊ” ናቸው፣ ነገር ግን ከክፉ መንፈስ የመጡ ናቸው!
ሲሚ ጆሮ ፍለጋ የሚሽቀዳደሙበትን እንደዚህ አይነት መናፍስታዊ ወረራዎች አይተን አናውቅም። ከሞቱ ሰዎች ጋር እንገናኛለን የሚሉ ሰዎችን በየቴሌቪዥን ትዕይንቶችም እናያለን። እነዚህ ሰዎች በእርግጥ ስላለፈው ጊዜ ግማሽ እውነት እና ስለመጪው ጊዜ ውሸት ከሚናገሩ ከሚታወቁ መናፍስት ጋር እየተነጋገሩ ነው። ይህ በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ በጥብቅ የተከለከለ ነው (ዘሌዋውያን 19፡31ን ተመልከት) ። እግዚአብሔር ወደ ጠንቋዮች እና ወደ መናፍስት ጠሪዎች በዞረ ሰው ሁሉ ላይ ፊቱን እንደሚያዞር ተናግሯል፤ (ዘሌዋውያን 20:6– 7 ን ተመልከት)፣ ሆኖም ግን ክርስቲያኖች አሁንም ኮከብ ቆጣሪዎችን እና መዳፍ አንባቢዎችን ይጠይቃሉ – ከዚያም ለምን ግራ መጋባት ውስጥ እንደሚኖሩ እና ሰላም እንደሌላቸው ያስባሉ።
በሕይወታችን ውስጥ ከራሱ ከእግዚአብሔር ውጭ ከየትኛውም ነገር መመሪያን መፈለግ ስህተት መሆኑን መገንዘብ አለብን። እንደዚህ ባሉ ድርጊቶች ላይ የተሳተፍክ ከሆነ በደንብ አድገህ ንስሃ እንድትገባ አሳስድሃለሁ፤ እግዚአብሔር ይቅር እንዲልህ ጠይቀው፤ ደግሞም ከእንደዚህ ዓይነት ልምምዶች ሙሉ በሙሉ ዘወር በል። የምትፈልጋቸው መልሶች ሁሉ ያሉት እግዚአብሔር ጋ ብቻ ነው።
ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡ ከክብሪቶች ጋር አትጫወት፤ ወደ እሳት ብቻ ይመራሉና።