በጭንቀት መሀል የጸሎትን አስተሳሰብ ማዳበር

በጭንቀት መሀል የጸሎትን አስተሳሰብ ማዳበር

በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ፣ከምስጋናም ጋር ልመናችሁን በእግዚአብሔር ፊት አቅርቡ እንጂ ስለማንኛውም ነገር አትጨነቁ፡፡ – ፊሊጲ 4፡6

በጫና ውስጥ ስትሆኑ ስለሁኔታው ከማውራት ይልቅ መጸለይ ይበልጥ ጥሩ ነው፡፡ ጸሎት የስኬታማ ህይወት ካርታ ነው፡፡ በምድር ህይወቱ ኢየሱስ ይጸልይ ነበር፡፡ ድርጊቶቹን እና ህይወቱን ጨምሮ ለእግዚአብሔር ሁሉንም ነገር በጸሎት ይሰጥ ነበር፡፡ እኛም እንደዛ ማድረግ እንችላለን፡፡ሁሉንም ችግሮቻችንን ለእርሱ ማስረዳት አይጠበቅብንም፡፡ ለእርሱ ሰጥተን ሁሉንም ነገር እንዲቆጣጠር መጠየቅ ብቻ ነው የሚጠበቅብን፡፡

ጸሎትን ላለማወሳሰብ ተጠንቀቁ፡፡ ብዙ ጊዜ ሰዎች የእውነት ከመጸለያቸው በፊት በማናቸውም ጊዜ ለመጸለይ እንደሚችሉ ካለመረዳት የተነሳ ከእግዚአብሔር ጋር ለብቻቸው ጊዜ እስኪያገኙ ድረስ ወይም ቤተ ክርስቲያን እስኪሄዱ ደረስ ይጠብቃሉ፡፡ በቀላል የእምነት ጸሎት ተማመኑ እና በፊሊጲሲዩስ 4፡6 ላይ የተሰጠውን የጳውሎስን ትዕዛዝ አስታውሱ፡፡ራሳችሁን በከባድ ሁኔታ ውስጥ ስታኙ በመጨነቅ ፈንታ ጸልዩ እና ከእግዚአብሔር ዕርዳታን ጠይቁ፡፡

መጽሀፍ ቅዱስ እግዚአብሔር ታማኝ እንደሆነ ይነግረናል-ይህ አንዱ ባህሪው ነው፡፡ ለእርዳታ ስንጸልይ ለእኛ ይመጣል ስለዚህም ሙሉ በሙሉ እና በተሟላ መልኩ በእርሱ መታመን አለብን፡፡ይህን ስናደርግ በመንገዳችን ለሚመጣ ለማንኛውም ነገር ዝግጁ እንሆናለን፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ ህይወቴን እየተጨነቅኩ መኖር አልፈልግም፡፡ዛሬ ራሴን ሁልጊዜ ወደ አንተ የመጸለይ ልማድ ውስጥ ለማስገባት ወስኛለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon