ባላችሁበት ዕስር ቤት እንኳ ለእግዚያብሔር ምስጋና ይሁን

ባላችሁበት ዕስር ቤት እንኳ ለእግዚያብሔር ምስጋና ይሁን

እኩለ ሌሊት አካባቢ ጳውሎስና ሲላስ እየጸለዩና እየዘመሩ እግዚአብሔርን ሲያመሰግኑ ነበር፤ ሌሎቹ እስረኞችም ያዳምጧቸው ነበር። 26ድንገትም የወህኒ ቤቱን መሠረት የሚያናውጥ ታላቅ የመሬት መንቀጥቀጥ ሆነ፤ ወዲያውም የወህኒ ቤቱ በሮች ተከፈቱ፤ የሁሉም እስራት ተፈታ። – ሐዋሥ 16፡25

አንዳንድ ጌዜ እጅግ በጣም ፋታ በማይሰጡ ነገሮች እንጠመዳለን፤ ለእራሳችንም ጊዜ አይኖረንም፡፡ ነገርግን እግዚብሔርን በእምነት መጠበቃችንን አጥብቀን ልንቀጥልና ልንገፋበት ይገባል፡፡ በዚህም እግዚያብሔር በድንገት ይመጣል፡፡

ጳውሎስና ሲላስ ስለመጠበቅ ያውቃሉ። ሐሥ 16 ጳውሎስና ሲላስ በብዙዎች መወገራቸውንና ወደ ወኽኒ ቤት መጣላቸውን ይነግረናል፡፡ ቁጥር 24 ላይ የእስርቤት ጠባቂው በምን አይነት ሰንሰለት እንዳሰራቸውና ጥፍንግ ተደርገው እንደታሰሩ ይነግረናል፡፡ ጳውሎስና ሲላስ ሁኔታውን ከምንም ሳይቆጥሩት መዘመርና ማምለካቸውን ቀጠሉበት፡፡ እግዚያብሔርን መጠበቃቸውን ቀጠሉ፡፡

ድንገትም እግዚያብሔር የመሬት መናወጥን አደረገ የወኅኒውም መሰረት ተናወጠ በሮቹም ተከፈቱ እርሱም ፈታቸው፡፡ በጣም አስቸጋሪ በሆነበት ወቅት ላይ ሰዎች እግዚያብሔርን መጠበቅ ሲጀምሩ እግዚያብሔር ያለንበትን ሁኔታ ይሰብረዋል፡፡ ስለዚህ ፈፅማችሁ ተስፋ እንዳትቆርጡ! ማመናችሁን እንዳታቆሙ! በተስፋ የተሞላችሁ ሁኑ፡፡ የእግዚያብሔር ኃይል ምን ገደብ የለበትም፡፡


ጸሎት ማስጀመሪያ

እግዚብሔር ሆይ ምንም ያህል በታላቅ ችግር ውስጥ ብሆንም እንኳን አንተን ማምለክና ማመስገኔን እቀጥላለሁ በዚዘ አልፈህ እንደምትመጣልኝ አውቃለሁ። እኔን ነፃ ለማውጣት ጊዜው ሲደርስ ድንገት ትመጣለህ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon