ብቻህን ከእግዚአብሔር ጋር ሁን

ብቻህን ከእግዚአብሔር ጋር ሁን

ሕዝቡን አሰናብቶ ይፀልይ ዘንድ ብቻውን ወደ ተራራ ወጣ፡፡ ማቴ 14÷23

ከእግዚአብሔር ጋር ጊዜ ለብቻ በፀጥታ ሥፍራ መሆን ለእኔ በጣም ጥሩ ነገር ነው፡፡ ለአንተም እንዲሁ ይሆናል ብዬ አምናለሁ፡፡ በቤቴ ውስጥ በየማለዳው ቀኔን ከመጀመሬ በፊት ከእግዚአብሔር ጋር የምገናኝበት የእራሴ ብር በቤቴ አለኝ፡፡ ከዚያም በተጨማሪ አራት ጊዜ በዓመት ከቤት ውጭ ሌላ ሥፍራ በመሄድ ጥቂት ቀናት ለብቻዬ የምሆንበት ወቅት አለኝ፡፡ በጸጥታ ውስጥ በፆምና በፀሎት ከእግዚአብሔር ጋር የረዘመ ጊዜ መውሰድ በጣም ያስደስተኛል፡፡

ብዙ ሰዎች በየዓመቱ እረፍት ለመውሰድና በየሳምንቱ ለመዝናናት እቅድ ያወጣሉ፡፡ የእራሳችንን ሚዛን ለመጠበቅ፣ ጤናማ ሕይወትና ስሜት እንዲኖረን ይጠቅማል፡፡ ነገር ግን በእውነቱ መንፈሳዊ እረፍት ደግሞ ከዚያ በበለጠ መልክ በማስቀደም በዓመታዊ ዕቅዳችንና በሳምንቱ ፕሮግራሞቻችን ልናኖር ይገባናል፡፡ ጊዜህን ለማንኛውም ነገር ከመመደብህ በፊት ለእግዚአብሔር ብትመድብ ምን ያህል እግዚአብሔርን እንደሚያከብር እለትህ አስብ፡፡ ኮንፍራንሶችን በአሜሪካና በውጭ ሀገራት ሳካሄድ በእነዚህ ኮንፍረንሶች ለአንዱ ወይም በሌላው ለመካፈል ከምሠራቸው የእረፍት ጊዜ የሚሞሉት የሰዎች ብዛት ስመለከት ሁልጊዜ እገረማለሁ፡፡ ስለእነርሱም አምላኬን አመሰግናለሁ፡፡ እግዚአብሔርም በምርጫቸው እንደሚኮራ አውቃለሁ፡፡ በመንፈሳዊ ሕይወታቸው ያድጋሉ፡፡ ምክንያቱም ከእግዚአብሐር ጋር ጊዜ ለማሳለፍ ከሕይወታቸው አንድን ነገር መስዋዕት አድርገዋልና፡፡

የሆነ ችግር ወይም አሳዛኝ እክል ገጥሞህ ከእግዚአብሔር ጋር ጊዜ እንድትወስድና ለችግርህ መልስ ወይም መፍትሔ በማግኘት እስኪያደርግህ ድረስ አትጠብቅ፡፡ እግዚአብሔር በመጀመሪያና በቀጣይነት ፈልግ ከዚያም በመንፈሳዊ ሕይወትህ ስለምትበረታ የሚመጣውን ነገር ሁሉ ማሸነፍ ትችላለህ፡፡ ኢየሱስን ለብቻው ከእግዚአብሔር ከአባቱ ጋር መሆን ካስፈለገ እኛንም ይልቁን ከእርሱ ጋር ለየብቻችን መሆን እንዴት አያስፈልገንም፡፡


የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ፡- አሁን በዚህ ሰዓት አጀንዳህን አውጣና ከእግዚአብሔር ጋር የተለየ ጊዜ የምትወስድበትን ፕሮግራም አውጣ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon