በመጽናትና መጽሐፍት በሚሰጡት መጽናናት ተስፋ ይሆንልን ዘንድ አስቀድሞ የተፃፈው ሁሉ ለትምህርታችን ተጽፈዋልና፡፡ ሮሜ. 15 4
ሁላችንም መበርታት እንፈልጋለን፡፡ አንዳንድ ጊዜ ከተስፋ መቁረጥ ጉድጓድ ውስጥ የሚያወጣን ማበረታቻ እንፈልጋለን፡፡ ነገር ግን አዎንታዊ ቃላት፣ የተስፋ ጭላንጭል ወይም ‹‹አንተ ማድረግ ትችላለህ! ›› የሚለንን መልዕክት እንፈልጋለን፡፡
እግዚአብሔር ራሱ የብርታት ምንጭ ነውና፣ እኛ ከእርሱ ብርታትና ተስፋ መፈለግ አለብን፡፡ እርሱ በመንፈሱ በኩል ያበረታታናል፡፡ ነገር ግን በቃሉ በኩልም የማበረታቻ ቃል ይናገረናል፡፡ ብዙ ጊዜ ብርታት ስፈልግ ወይም ጉልበቴ በተስፋ እንዲታደስ ስፈልግ፣ ወደ መጽሐፍ ቅዱስ እሄዳለሁ፡፡ ከመጽሐፍ ቅዱስ ንባቦች ውስጥ ብርታትና እርዳታ ጉልበት ስፈልግ በቃል የማሰላስለው የመጽሐፍ ክፍል አለኝ፡፡
የእግዚአብሔር ቃል በማበረታቻ ተስፋዎች የተሞላና መጽሐፍ ቅዱስን ባነበብነው ልክ የማበረታቻ መድኃኒት እናገኛለን፡፡ አንድ የእግዚአብሔር ቃል ትርጉም (ፍቺ) ለጥያቄአችን መድኃኒት ነው፡፡
ለመበረታታት በምትፈልግበት ወቅት ወደ እግዚአብሔር ቃል ሂድ፡- ተስፋ ስትቆርጥ፣ ስትጎዳ፣ ቅር ስትለኝ፣ ግራ ሲገባህ፣ ስትዝል፣ ቃሉ ወደ ልብህና ወደ አእምሮህ እንዲጠልቅ በማድረግ በእግዚአብሔር መገኘት ውስጥ እንድትገባ ቃሉን አሰላስል፡፡ እግዚአብሔር አይጥልህምና በቃሉ ሁልጊዜ ልትታመን ትችላለህ፣ በተለይ ብርታትና ተስፋ ማግኘት ሲያስፈልግህ፡፡
ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- ዛሬ የምታደርገው ምንም ችግር የለውም፣ ነገር ግን በተስፋ አጽንተህ ያዘው፡፡