ተጨባጭ ነገር

ተጨባጭ ነገር

ከክፉ ሽሽ መልካምንም አድርግ ሠላምን እሽ ተካላትም፡፡ መዝ 34÷14

ሠላምን ልክ እግዚአብሔርን እንደምንከተል ልንከተል እንደምንገባ መከተል እንዳለብን ብዙውን ጊዜ አስተምራለሁ፡፡ ነገር ግን ስለ እውነት ያልሆነ ሰላም መረዳትና መንቃት እንዳለብን ነው፡፡ ለምሳሌ አንድን ለማድረግ ትልቅ ጉጉት ሲያድርብን የውሸት ሠላም ከስሜታችን የሚመነጭ ለጊዜው ሊፈጥርብን ይችላል፡፡ ትንሽ ጊዜ እያለፈ ሲመጣ ያ ሠላም እየጠፋ ይሄድና የእግዚአብሔር የሆነው መገለጥ ይጀምራል፡፡ ለዚህም ወሳኝ የሆኑ ውሳኔዎች ላይ በጣም ፈጥነን ወደ ውሳኔ ማምጣት የለብንም፡፡ ለጥቂት ጊዜ መጠበቅ ሁልጊዜ ጥበበኝነትና ጠንቃቃነት ነው፡፡

ለምሣሌ አንድ ወቅት እኔና ባለቤቴ ዴቭ (ዳዊት) አንድ በጣም የምንወደው ሰው በችግሩ ልንረዳው አሰብላ፡፡ ከዚያ የሰውዬውን ፍላጎት ስለማለን በጣም ከመደሰቱ የተነሣ እኛም ለጊዜው በጣም ተደስተን፡፡ በእቅዳችን መሠረት እየቀጠልን እያለን ሠላማችን በነገሩ በቀጠልን መጠን ሠላማችን ቀንሶ መጣ፡፡ ከዚህም የተነሣ ችግር ተፈጠረ ምክንያቱም ተስፋ የገባነው ሰውዬውን በቀጣይነት ለመረዳት ቃል ስለገባን ቃሉን ማጠፍ ከበደብኝ፡፡ ሰውዬውን በእኛ ተስፋ አድርጎ ነበርና፡፡

ለተወሰኑ ሳምንታት በጉዳዩ ላይ ስፀልይ ቆየው፡፡ ውሎ እያደር ሰላሜን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየነሣኝ ስለመጣ ወደ ሰውዬው ሄጄ ስለዕቅዳችን አንድ ነገር ትክክል እንዳልሆነ ይሰማኛል፡፡ እኔ ፈፅሞ ሰላም በጉዳዩ እየተሰማኝ አይደለምና ችግሬን ማቃላል የምችለው እውነታውን ለአንተ መግለፅ ነውና ስለው እርሱም በተመሳሳይ ችግር ውስጥ እንዳለ ገለፀልኝ፡፡ ይህ ለጊዜው የመሰጠኝ የውሸት ሰላም ጥቅት ጊዜ ቆይቶ የሚጠፋ ወደዚህ ትልቅ ዕቅድ ውስጥ ከተተኝ፡፡


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- ትላልቅ ውሳኔዎችን ከማድረግህ በፊት ትክክለኛ የሆነ ልብን የሚሞላ ሰላም እስኪሰማህ ድረስ ፈጥነህ አትወስን፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon