የከበደህን ነገር በእግዚአብሔር ላይ ጣል፤እርሱ ደግፎ ይይዝሃል፤የጻድቁንም መናወጥ ከቶ አይፈቅድም። – መዝሙር 55፡22
እግዚብሔር ከእናንተ ጋር ልውውጥ መፈፀም እንደሚፈልግ ታውቃላችሁን? ያላችሁን ሁሉንም ጭንቀት ፣ ችግር እና ውድቀት ሁሉ ለእርሱ እንድትሰጡት ይፈልጋል በምላሹ ሰላምና ደስታን ይሰጣችኋል፡፡
እግዚያብሔር ስለዕኛ ግድ ይለዋል ነገርግን ይህ እንዲሆን ስለራሳችን መጨነቅና ከሚገባው በላይ ማሰብ ማቆም ይኖርብናል፡፡ ብዙ ሰዎች እግዚያብሔር ስለእነሱ እንዲያስብላቸው ይሻሉ ነገርግን እግዚያሔርን ከመጠበቅ ይልቅ ስለራሳቸው አብዝተው በመጨነቅ ለጥያቄዎቻቸውና ችግሮቻቸው በራሳቸው መንገድ ምላሽን ሲፈልጉ ይታያሉ፡፡
ፈርሃታችንን ለእርሱ ስናስረክብ እግዚብሔር ሰላሙን ይሰጠናል፡፡ ምን አይነት ታላቅ ንግድ ነው ፍርሃታችንን ለእግዚያብሔር እንሰጣለን እርሱ ደግሞ ሰላሙን ይሰጠናል፡፡ ስለዕኛ ያለንን መጨነቀና ፍርሀት ለእርሱ እንተዋለን እርሱም ሰላሙንና ጥበቃውን ያደርግልናል፡፡ ይህ እጅግ በጣም አስደሳችና የሚገርም ዕድል ነው፡፡
ጸሎት ማስጀመሪያ
እግዚያብሔር ሆይ ታላቅ የሆነ የልውውጥ ጥያቄን አቅርበህልኛል ፤ ከእኔም በላይ ነህ። ስለእኔ የማስበውንና የምጨነቀውን ሁሉ ለአንተ በመተው ሰላምና ደስታህን እቀበላለሁ፡፡