ትሁታን እርዳታውን ያገኛሉ

ትሁታን እርዳታውን ያገኛሉ

እንግዲህ በጊዜው ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከኃይለኛው ከእግዚአብሔር እጅ በታች ራሳችሁን አዋርዱ፡፡ – 1 ጴጥ 5፡6

ኢየሱስ የሚያስጨንቀንና የሚያሳስበንን ነገሮች ሁሉ በእርሱ ላይ እንድንጥለው ይጋብዘናል፡፡ አብዛኛዎቻችን ይህን ለማድረግ ፈቃደኛ ያልሆነው ለምንድን ነው? የጭንቀትን ሸክም ስንሸከም ምን ያህል እንደምንሰቃይ አንገነዘብ ይሆናል፡፡

በህይወታችን ውስጥ ድል የሚገኝበት ብቸኛው መንገድ የእግዚአብሔር ጥበብን መከተል ነው፡፡ ሰላምን የምንፈልግ ከሆነ መጨነቅን ማቆም አለብን፡፡ የሚያሳስበን ነገር በመንገዳችን ላይ ሲመጣ የእግዚአብሔር እርዳታ ያስፈልገናል፡፡ ይህንን እርዳታ እንዴት ልናገኝ እንችላለን ሲባል  1ጴጥ 5፡6 ላይ ራሳችንን በትህትና ዝቅ ማድረግ አለብን ይለናል፡፡

ይህ በጣም ግልጽ እና ቀላል ይመስላል ሆኖም ግን አንዳንዶች ይህንን እርዳታ ላለመጠየቅ ከመጠን በላይ ግትር ሆነው ይታገላሉ:: ነገር ግን ትሁታን የእግዚአብሔርን እርዳታ ያገኛሉ፡፡ ስለዚህ የአንተ መንገድ ካልሰራልህ ለምን የእግዚአብሔርን መንገድ  አትሞክረውም? እራሳችን በትህትና አዋርደን እግዚአብሔርን ለእርዳታ ስንጠይቀው በሁኔታችን ላይ ኃይሉን ይገልጣል፡፡ የዚያን ጊዜ ብቻ ነው በሕይወት መደሰት የምንችለው፡፡ ስለዚህ ዛሬ ራስህን በእግዚአብሔር ፊት አዋርድ እርሱም ሸክምህን/ ጭንቀትህን ይወስድልሃል፡፡


ጸሎት ማስጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ ሐይወቴን በራሴ በሰላም መያዝ አልችልም፡፡ ስለዚህም ራሴን ትሁት አድርጌ የአንተን እርዳታ እጠይቃለሁ፡፡ አምንሃለሁ ሕይወቴንም እንድትቆጣጠረው እሰጥሃለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon