ትክክለኛዉን ሐሳብ ተቀበል

ትክክለኛዉን ሐሳብ ተቀበል

በእግዚአብሔር ዕዉቀት ላይ በትዕቢት የሚነሳዉን ክርክረና ከንቱ ሀሳብ ሁሉ እናፈርሳለን፤ አእምሮንም ሁሉ እየማረክን ለክርስቶስ እንዲታዘዝ እናደርጋለን፡፡ – 2 ቆሮ 10፡5

ንደ ክርስቲያኖች ወደ አእምሮአችን የሚመጡትን ሀሳቦች ሁሉ መቀበል የለብንም፡፡ በምትኩ በቅዱስ ቃሉ መለኪያ ልክ ከላይ ያለዉ ጥቅስ እንደሚነግረን መፈተሽ አለብን፡፡

ተግባራዊ ምሳሌ ይኸዉና፦ አንድ ሰዉ ስሜታችሁን ቢጎዳዉ ወዲያዉ ዉሳኔ አድርጉ ከዚያ ስትብሰለሰሉ አትዉሉም፡፡ ከእናንተ ጋር ሲቆይ ብቻ ነዉ ሰይጣን የጥላቻን ዘር እንዲዘራ ዕድል የሚያገኘዉ፡፡

በምትኩ አሉታዊ አስተሳሰብ አስወግዳችሁ ሰላማችሁና ደስታችሁ እንዳይጠፋ ማድረግ ትችላላችሁ፡፡

ወደ እግዚአብሔር ቀርባችሁ እንዲህ በሉ “አባት ሆይ እንድታበረታኝ እፈልጋለሁ፤ የበደሉኝን ይቅር እል ዘንድ ጸጋህን ልቀበል በእምነት መርጬአለሁ፤ እንድትባርካቸዉ እጠይቅሃለሁ፤ ህይወቴን ወደ ፊት እንድቀጥል እርዳኝ፤ በኢየሱስ ስም አሜን”

አእምሮአችን በእግዚአብሔር ቃል እንደተለወጠ አስተሳሰባችንም ተቀይሮ በቅዱሳት መጽሓፍት መስመር ይሄዳል፡፡ ከዚያ ቀን በቀን በሀሳቦቻችን ዙሪያ እግዚአብሔራዊ ወሰኖች ይመሰረታሉ፡፡ ይህ ወሰን የጠላትን ሽንገላ እንድትቋቋሙ መርዳት ብቻ ሳይሆን የበለጠ ጣፋጭ እግዚአብሔራዊ ህይወት እንድትኖሩ ይረዳችኋል፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

ጌታ ሆይ! ካንተ ሀሳብና ከቃልህ ጋር የሚሄዱ አስተሳሰቦችንና ንግግሮችን ብቻ መቀበል እፈልጋለሁ፡፡ ጠላት ወደ እኔ ክፉ ሀሳቦችን ሲያመጣ መንቃት እንድችልና ቃልህ የሚለዉን ብቻ ማድረግ እንድችል እርዳኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon