በመካከላችሁ ሳለሁ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር እርሱም እንደተሰቀለ ሌላ ነገር እንዳላውቅ ቆርጬ ነበርና። – 1 ቆሮ 2፡2
በርካታ ክርስቲያኖች ከእግዚአብሔር ቃል ይልቅ ዓለማዊ ዕውቀትን በመፈለግ ሩጫ ሲባክኑ ይታያል፡፡ የእግዚአብሔር ቃል እራሱ ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሳ ጠፍቷል ይላል (ሆሴ 4፡6)፡፡
ጳውሎስ የአእምሮ ዕውቀት ያካበተ የተማረ ሰው ነበር፡፡ ከሌሎች በጣም የተሻለ ሰው እንደሆነ ያስብ ነበር፡፡ ክርስቲያኖችን ለመግደል ይፈልግ ነበር፡፡ ደግነቱ እግዚአብሔር ለዚህ ሰው ሌላ ዕቅድ ነበረው ፤ ሕይወቱን በዘላቂነት ሊቀይር በሚችል መንገድም ራሱን ገለጠለት።
ጳወሎስ ሥጋዊ እውቀት ፍለጋ ከመንፈሳዊ እውቀት አስፈላጊነት ጋር የማይወዳደር መሆኑን ሲረዳ በተቃራኒው ይህንን መንፈሳዊ ዕውቀት ለመፈለግ ወሰነ፡፡
ልክ እንደ ጳውሎስ መንፈሳዊ ነገሮችን መማር ያለውን አስፈላጊነት መረዳት አለብን፡፡ ዓለማዊ ነገሮችን ከመፈለግና አእምሯችንን ጠቃሚ ባልሆኑ ነገሮች ከመሙላት ይልቅ የእግዚአብሔርን ቃል ማንበብ፣ ማጥናትና ቃሉን በማሰላሰል አእምሯችንን በእግዚአብሔር ቃል መሙላት አለብን፡፡
የእግዚአብሔርን ቃል ማወቅ ሕይወታችሁን ሊቀይር እንደሚችል ከልምዴ ልነግራችሁ እችላለሁ፡፡ ቃሉ ጳውሎስን ማንም ኖሮት የማያውቅ ዓይነት ክርስቲያን አድርጎ ቀይሮታል፡፡ ቃሉ እናንተንም የመለወጥና በክርስቶስ ውስጥ ባገኛችሁት አስደናቂ ፍጸሜ የመምራት አቅም አለው፡፡
በቃሉ ውስጥ የሚገኘውን መንፈሳዊ ዕውቀት እንድትፈልጉ ዛሬ አበረታታችኋለሁ፡፡ የእግዚአብሔር ቃል በልባችሁና በአእምሯችሁ ውስጥ ሲሞላ የምትፈልጉትን ነገር እንድታገኙ ይረዳችኋል፡፡
ጸሎት ማስጀመሪያ
እግዚአብሔር ሆይ ያለኝን ሁሉ ልሰጥህ እፈልጋለሁ፡፡ ራሴን ህያው መስዋዕት አድርጌ አቀርባለሁ፡፡ ለራስህ ክብር የሰጠኸኝን ሃብት እንዴት ልትጠቀምበት እንደምትፈልግ አሳየኝ፡፡