በእኔ ሰላም እንዲኖራችሁ፣ይህንን ነግሬያችኋለሁ፡፡በአለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ነገር ግን አይዟችሁ ፤እኔ አለምን አሸንፌዋለሁ፡፡ – ዮሐ 16፡33
የተረጋጋ እና ሰላማዊ አመለካከት እጅግ ውድ ነገር ነው፡፡እንዲህ ያለው አመለካከት “በእግዚአብሔር ላይ እተማመናለሁ” የሚል እና ለሰዎች በሀይል ተሞልቶ የሚናገር ነው፡፡በዘላቂነት የሰላም ሰው ለመሆን ግን ጊዜ፣ትኩረት እና የእግዚአብሔርን ጸጋ ይፈልጋል፡፡
ብዙ ጊዜ የጭንቀታችን መጠን ከሁኔታዎቻችን ጋር የተሳሰረ ነው፡፡ጊዜ ስለሌላችሁ፣የገንዘብ ችግር ስላጋጠማችሁ ወይም ከምትወዱት ሰው ጋር አብሮ መቐጠል ስላልቻላችሁ ልትጨናነቁ ትችላላችሁ፡፡
በህይወታችን ያለውን ጭንቀት ለማሸነፍ በክርስቶስ የማሸነፍ ሀይል የተሰጠንን ሰላም መጠቀምን መማር አለብን፡፡
አንዱ ዘላቂ ሰላም ማዳበሪያ መንገድ “አሁንን” መኖር ነው፡፡ያለፈውን ህይወታችንን በማሰብ እና ወደፊታችን ምን እንደያዘልን በመጨነቅ ብዙ ጊዜ ልናሳልፍ እንችላለን…አዕምሯችን ዛሬ ላይ ካላተኮረ ግን ምንም ነገር ማከናወን አንችልም፡፡
መጽሀፍ ቅዱስ ሲናገር ለእያንዳንዱ ለምንኖረው ቀን እግዚአብሔር ጸጋ ሰጥቶናል፡፡ማድረግ ያለብንን ለማድረግ የሚያስችለን እና ሀይልን የሚሞላን ጉልበት በሚያስፈልገን መጠን ሳይሰስት በልግስና የሰጠን የእግዚአብሔር ጸጋ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡
በእያንዳንዱ ቀን “እግዚአብሔር ዛሬን ሰጥቶኛል፡፡እደሰትበታለሁ፣ሀሴትም አደርግበታለሁ” ማለት አለብን፡፡
ጸጋውን በፈለጋችሁት መጠን እየተቀበላችሁ “በአሁናችሁ” ላይ ጌታን መታመን ከተለማመዳችሁ እውነተኛ የሰላም ሰው ትሆናላችሁ-ይሄም በጣም ሀይለኛ ነገር ነው፡፡
የጸሎት መጀመሪያ
እግዚአብሔር ሆይ ማናቸውንም እና ሁሉንም አይነት እንቅፋት እንዳሸነፍከው ስለማውቅ ለእኔ በሰጠኸኝ ሰላም ውስጥ እንድኖር እንድትረዳኝ እጸልያለሁ፡፡ “አሁኔን” ስኖር እንዴት በአንተ መታመን እንዳለብኝ አሳየኝ፡፡