ንጉሱም መልሶ ፣እውነት እላችኋለሁ፣ከእነዚህ አነስተኛ ከሆኑት ወንድሞቸ ለአንዱ ያደረጋችሁት ፣ለእኔ እንዳደረጋችሁት ነው ይላቸዋል፡፡ – ማቴ 25፡40
አንዴ ሩሲያ ውስጥ ቤመንገዱ እየዞረ “ኢየሱስ ይወዳችኋል፡“ ኢየሱስ ይወዳችኋል፡፡”እያለ ትራክት ሲያድል አንዲት ሴት “ታውቃለሁ፣ስብከትህ እና ትራክትህ እኮ ሆዴን አይሞሉትም” ስላለችው ወንጌላዊ አንድ ታሪክ ሰምቼ ነበር፡፡
ይሄ ታሪክ አንድ አስፈላጊ ነጥብን ያሳያል፡አንዳንድ ጊዜ ለሰዎች የእግዚአብሔርን ፍቅር የምናሳየው አካላዊ ፍላጎቶቻቸውን ከሞላንላቸው በኋላ የክርስቶስን ወንጌል በመስበክ ነው፡፡
ኢየሱስ የሰዎችን አካላዊ ፍላጎት ስለሟሟላት አስፈላጊነት ተናግሯል፡፡ማቴዎስ 25 ላይ የተራቡትን ስንመግብ፣ወይም የተጠሙትን ውሃ ስናጠጣ፣ወይም የታረዙትን ስናለብስ፣ወይም የታመሙትን ስናስታምም እነዚህን ነገሮች ለእርሱ እንዳደረግን ነው የሚቆጠረው፡፡አንድን ሰው ተግባራዊ በሆነ መንገድ መርዳት ወንጌልን ለእዛ ሰው ለማካፈል ድንቅ የሆነን አጋጣሚ እንደሚፈጥርልን አሳይቶናል፡፡
አንድ ሰው በራሱ ሕይወትየእግዚአብሔርን ፍቅር በእውነተኛ መንገድ በስራ ላይ ሲያየው እግዚአብሔር ይወድሀል የሚለውን መልዕክታችንን ለማመን የበለጠ ይቀለዋል፡፡
ታዲያ ይሄ በተግባር ምንድነው የሚመስለው?አልወደድም ብሎ የሚያስብን አንድ ሰው አቅፎ ሰላም እንደማለት ባለ ትንሽ በሆነ ነገር መጀመር ይቻላል፡፡ከዛ የታመሙን፣የተጠሙትን እና የተራቡትን የሚደግፉ አገልግሎቶችን በመርዳት መቀጠል ነው፡፡ምናልባት ምግብ በሚረዳ ወይም ሌሎችን በሚደርስ በሰፈራችሁ ያለ አገልግሎት ውስጥ የበጎ ፈቃድ ሰራተኛ ልትሆኑ ትችላላችሁ፡፡ወይም በሌላ አገር ወዳሉ እርዳታ የሚፈልጉ ሰዎች ሚስዮናዊ ጉዞ ልታደርጉ ትችላላችሁ፡፡ሌሎችን በቃል ብቻ ሳይሆን በተግባራዊ ድርጊት ለማገልገል ስትወስኑ አማራጮቹ ብዙ ናቸው፡፡
የጸሎት መጀመሪያ
ጌታ ሆይ ቃላቶቼ በድርጊት እንዲታጀቡ እፈልጋለሁ፡፡በመንገዴ የምታመጣቸውን ሰዎች የፍቅርህን ሀይል ይለማመዱ ዘንድ በተግባራዊ መንገድ እንዴት ልረዳቸው እንደምችል አሳየኝ፡፡