አንጥረኛችን

አንጥረኛችን

«… እርሱም ብርን እንደሚያነጥርና እንደሚያጠራ ሰው ይቀመጣል፥ የሌዊንም ልጆች ያጠራል፥ እንደ ወርቅና እንደ ብርም ያነጥራቸዋል፤ እነርሱም ለእግዚአብሔር በጽድቅ ቍርባንን የሚያቀርቡ ይሆናሉ» (ሚል.3፡ 3)

ለዓመታት ወደኋላ መለስ ብዬ ስመለከት ከእግዚአብሔር ጋር የነበረኝ የህይወት ጉዞ እጅግ አስደናቂ እንደነበር መመልከት እችላለሁ። እርሱ በሙላት ለውጦኛልና አሁንም በየእለቱ እየለወጠኝ ይገኛል። በነፍሴ ማለትም በአዕምሮዬ፣ በስሜቴና በፈቃዴ፤ እንዲሁም የመንፈስ ቅዱስን ሙላት በተቀበልኩበት ጊዜ በዙሪያዬ ብዙ ችግሮች ነበሩኝ።ከጥቂት ጊዜ በኋላ ያረጋገጥኩት ነገር በህይወቴ ምን እየተከናወነ እንደሆነ ነው። እግዚአብሔርን ስለለውጥ ለምኜው ነበር፤ ነገር ግን እኔ ሙሉ በሙሉ ያላወቅሁት ነገር በህይወቴ መለወጥ የነበረበት ነገር እኔ ነበርኩ።

እግዚአብሔር በህይወቴ ለውጥን ጀምሮ በሂደት ላይ ነበር፤ በዝግታ፣ በጽናትና ሁልጊዜ እኔ ለመታገስ በምችልበት ፍጥነት ላይ ነበር። እንደ አንጥረኛ፣ እርሱ በእሳት ላይ አስተምጦን በህይወታችን ላይ መቃጠል ያለበትን እያቃጠለ ፈጽሞም ብዙ ሳያቃጥልና ፈጽሟም እንዳይሞቱ እርግጠኛ ነበር። እኛ ወደ እርሱ እሳቱ ሲያጠፋው እኛ ሲመለከትና የእርሱን ምስል በእኛ ያያል።እናም ከዚያም የጊዜ አማራጭ በመፈለግ እንቀጥላላልን።

እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ስለ ትዕግስት ሲሞግት፣ እኔ በትክክለኛ ትዕግስት አስተናግዳቸዋለሁ ወይስ በክፉ ላስተናግዳቸው እንደምችል ብዙ ተግዳሮቶች ይጋፈጡኛል። ብዙውን ጊዜ እኔ የማስተናግዳቸው በከፋ መንገድ ነው። ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ ይወቅሰኛል፣ ያስተምረኛል፣ እንዲሁም ለእግዚአብሔር ክብር መኖር እንድችል በውስጤ መሻቱን ይሰጠኛል። በሂደት ቀስ በቀስ በአንድ የህይወቴ ገጽታ ላይ ለውጥ አያለሁ፤ ቀጥሎ በሌላው ላይ ይከተላል። እኔ ብዙውን ጊዜ በሚያጋጥሙኝ ውጊያዎች መካከል ለጥቂትም ቢሆን አረፍት እፈልጋለሁ።


የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ፡ በህይወትህ ለውጥ የሚያስፈልገውን የህይወትህን ክፍል እግዚአብሔር ሲያሳይህ ፈጽሞ ተስፋ አትቁረጥ።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon