አዎንታዊ አስተሳሰቦችን ለማሰብ ነጻ መሆን

አዎንታዊ አስተሳሰቦችን ለማሰብ ነጻ መሆን

አምላካችን መጠጊያችንና ሀይላችን፣በሚደርስብን መከራ ሁሉ የቅርብ ረዳታችን ነው፡፡ስለዚህ ምድር ብትነዋወጥ እንኳ ተራሮችም ወደ ባህር ጥልቅ ቢሰምጡ አንፈራም፡፡ – መዝ 46:1-2

በህይወቴ በጣም ብዙ ማዕበሎችን ተጋፍጫለሁ-አንዳንዶቹ እንደ በጋ ወቅት ፈጣን የከሰዐት በኋላ ማዕበሎች ሲሆን አንዳንዱ ደግሞ እንደ ደረጃ አራት ማዕበል ነው!

ስለእነዚያ ማዕበሎች የተማርኳቸው ነገሮች ቢኖሩ ዘላለም እንደማይቀጥሉ እና በእነርሱ ውስጥ ሆኜ ደግሞ አቢይ የሚባል ውሳኔ መወሰን እንደማያስፈልገኝ ነው፡፡

በችግሮች መሀል ሀሳቦችና ስሜቶች ይመላለሳሉ ነገር ግን ውሳኔ ለማሳለፍ መጠንቀቅ ያለብን ጊዜያት እነዚህ ናቸው፡፡ለእራሴ ከመወሰን በፊት ስሜት ይረጋጋ ብዬ አስባለሁ፡፡

ማድረግ የምንችለው ላይ ለማተኮር እና ማድረግ ለማንችለው እግዚአብሔር ን ለመታመን መረጋጋት እና ራሳችንን ስርዐት ማስያዝ አለብን፡፡

በጭንቀት እና በፍርሀት ውስጥ ከመስመጥ ይልቅ ያሳለፋችሁትን ማዕበል እና የምትደርሱበትን ትልቁን ስዕል ከሚያየው ከእግዚአብሔር ጋር ተገናኙ፡፡ በህይወታችን መሆን ያለበት ነገር ሁሉ በትክክለኛው ጊዜ መሆኑን፣በትክክለኛው ፍጥነት እየሄደ መሆኑን እና ወዳቀደልን መድረሻችን በደህና መድረሳችንን እግዚአብሔር ያረጋግጥልናል።


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ ሁሉን ነገር መቆጣጠር እንደማልችል አውቃለሁ፡፡ማድረግ የምችለውን አደርጋለሁ ማድረግ የማልችለውን አንተ እንደምታደርገው አምንሀለሁ፡፡የህይወት ማዕበል አይቆጣጠረኝም፡፡ለእኔ ያሉህን እቅዶች አምናቸዋለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon