አዎንታዊ አስተሳሰቦችን ለማሰብ ነጻ መሆን

በልቡ እንደሚያስብ እንደዛው ነው፡፡ – ምሳ 23፡7

ይህ ጥቅስ ጤናማ፣አዎንታዊ አስተሳሰቦችን ስለራሳችን ማሰብ እንዴት አስፈላጊ እንደሆነ ያሳየናል፡፡ሁልጊዜ የምታስቡት አሉታዊ ሀሳቦችን ከሆነ ህይወትን ልትወዱ አትችሉም፡፡በዚህ ነገር የምትቸገሩ ከሆነ የምታስቡበትን መንገድ ለመቀየር እንድትሰሩ አበረታታችኋለሁ፡፡አዎንታዊ ሀሳቦችን የሚያስብ ሰው መሆን ምርጥ መንገድ ሆኖ ያገኘሁት ለብዙ እርዳታ ወደ እግዚአብሔር መቅረብና ደጋግሞ መጠየቅ ነው፡፡

ችግር እንደሆነ አምኖ ከእግዚአብሔር እርዳታ መጠየቅ ከአሉታዊ አስተሳሰብ ለመላቀቅ ትልቁ እርምጃ ነው፡፡ነገር ግን አንድ ጊዜ ይህን ካደረጋችሁ በኋላ ማሸነፍ ትችላላችሁ ምክንያቱም መጽሀፍ ቅዱስ እንደሚለው በክርስቶስ አዲስ ሰው ናችሁ (2 ኛ ቆሮ 5፡17)፡፡

ብዙ ሰዎች በህይወት ብዙ ከመጎዳታቸው የተነሳ ተስፋ ማድረግን ይፈራሉ፡፡ፍልስፍናቸውም ”ምንም አይነት መልካም ነገር ያጋጥመኛል ብዬ ካልጠበቅሁ ሳይሆን ሲቀር አላዝንም”የሚል ነው፡፡

የማስበው እንደዛ ነበር፡፡ብዙ ሀዘንን ስላስተናገድሁ አዎንታዊ በሆነ መንገድ ማሰብ ያስፈራኝ ነበር፡፡የእግዚአብሔርን ቃል ማጥናት ስጀምርና እግዚአብሔር ወደ ትክክለኛ አቋም እንዲመልሰኝ ስታመንበት አሉታዊ አስተሳሰቦቼ መሄድ እንዳለባቸው ገባኝ፡፡

በሁሉም ሁኔታ ውስጥ አዎንታዊ አስተሳሰብን መለማመድ አለብን፡፡በአስቸጋሪ ጊዜ ውስጥ እያለፋችሁ ከሆነ እግዚአብሔር ነገሮችን ለእናንተ ለመልካም እንደሚቀይራቸው ጠብቁ፡፡እንደ ክርስቲያን ስለ አስተሳሰባችሁ ለመዋጋት ጊዜው ነው ምክንያቱም አዕምሯችሁ በአንዴ ከእግዚብሔር ዕቅዶች ጋር መስማማት አይችልም፡፡

የእግዚአብርን ቃል በመመርመር ከእናንተ አስተሳሰብ ጋር እያነጻጸራችሁ ጊዜን እንድታሳልፉ አበረታታችኋለሁ፡፡እግዚአብሔር አስተሳሰባችሁን ከራሱ አስተሳሰብ ጋር እንዲያስማማው ጊዜን ስጡት፡፡እንዴት የበለጠ አዎንታዊ ሀሳብ የሚያስብ ሰው መሆን እንደምችል አሳይቶኛል እናንተንም እንዴት መሆን እንደምትችሉ ያሳያችኋል፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ ከአሉታዊ አስተሳሰብ ጋር እንደምታገል እና እርዳታህ እንደሚያስፈልገኝ አምናለሁ፡፡አስተሳሰቤን ከቃልህ ጋር አስማማልኝ፡፡በእያንዳንዱ ሁኔታ ነገሮችን ለእኔ መልካም ለሆነ ነገር እንደምታደርገው አሳስበኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon