አጽናኝ

የማጽናናችሁ እኔ ነኝ፣ እኔ ነኝ፣ ኢሣ 51 12

አብዛኛዎቹ የመንፈስ ቅዱስ ስሞች ብዙውን ጊዜ በእኛ ሕይወት ውስጥ ያለው አገልግሎት የእርሱን ባሕሪና ማንነት የሚገልጹ ናቸው፡፡ እርሱ የእኛ አስተማሪ፣ ረዳት፣ አማላጅ ጠበቃ፣ አበረታች፣ አንቂ ይባላል፡፡ እነዚህ ስሞች የሚያመለክቱት መንፈስ ቅዱስ በአማኝ ሕይወት ውስጥ የሚሠራውን ነው፡፡ ዛሬ ለማተኮር የምፈልገው የእኛ አጽናኝ በሆነው ላይ ነው፡፡ (ዮሐ 14 6 ተመልከት) ለብዙ ዓመታት በመደበኛነት ከባለቤቴ ጋር እጣላ ነበር፡፡ ምክንያቱም ስወድቅና አጽናኝ ስፈልግ ስለማያጽናናኝ ነው፡፡ በእርግጥ እርሱ የበኩሉን ይሞክራል፡፡ ነገር ግን ያስተዋልኩት ነገር ቢኖር እግዚአብሔር ራሱ (ዴቭ ባለቤቴ) እንዲያጽናናኝ አይፈቅድም፡፡ ምክንያቱም በእርሱ ፋንታ የመንፈስ ቅዱስን ማጽናናት መፈለግ ስላለብኝ ነበር፡፡ እርሱ (መንፈስ ቅዱስ) የሚያስፈልገኝን መጽናናት ሁሉ በቀላሉ ስጠይቅ ይሰጠኛል፡፡

እግዚአብሔር ሰዎች ለእኛ የተወሰነ መጽናናት ለእኛ እንዲደርጉ ይፈቅዳል፡፡ ከዚያ በላይ ሊያደርጉ አይችሉም፡፡ ከመጠን በላይ የሚያቀርቡን ሰዎች የሚያስፈልገንን ነገር ሁልጊዜ ሊሰጡን ወይም ሊያደርጉልን አይችሉም፡፡ እግዚአብሔር ብቻ ሊያደርግልን የሚችለውን ከሌሎች ሰዎች ስንጠብቅ የእኛ መሻት የተሳሳተ ቦታ ይወድቅና እኛም ሁልጊዜ በቅሬታ ውስጥ መውደቅ ይሆናል፡፡

የእግዚአብሔር ማጽናናት በብዙ ነገር ከማንኛውም ማጽናናት ይበልጣል፡፡ ማንም ሰው እኛ የምንፈልገውን ነገር በእርግጥ ሊያደርግልን አይችልም፡፡ ምናልባት እግዚአብሔር ያንን ሰው እንዲያገለግለን ቀበቶ ያላነሳልን ካልሆነ አይሆንም፡፡ እግዚአብሔር ብቻ እውነተኛ የመጽናናት ምንጫችን ነው፡፡ ለእኛ የሚመቸውን ነገር ለእኛ እንዲልክልን ወደ እርሱ በሄድ መቀበል አለብን፡፡ ዛሬ ተጎድተህ ቢሆን እግዚአብሔር መለኮታዊ መጽናኛ እንዲሰጥህ እንድትጠይቅ አበረታታሃለሁ፡፡


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- ከእግዚአብሔር መጽናናትን በመፈለግ ተቀበል፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon