አፍህን ይሞላዋል

አፍህን ይሞላዋል

የልብ መዘጋጀት ከሰው ነው፣ የምላስ መልስ ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው፡፡ ምሳ 16÷1

አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔር ካሰብነው ሃሳብ ውጭ ይናገረናል፡፡ ይህንንም የተማርኩት ትልቅ ውሳኔ ለመወሰን በምቸገርበትና የእግዚአብሔር እርዳታ በሚያስፈልገን ወቅት ነበር፡፡ ነገር ግን የእግዚአብሔር ምርት ከእኔ ጋር ያለ አይመስለኝም፡፡ የእራሴ ሃሣብ ግራ አጋብቶኛል፡፡ ምንም ለውጥና ዕድገት እያሳየሁ አይደለም እኔና ወዳጅ አብረን እየተጓዝን እያለ፡፡

በጉዳዩ ላይ እኔና ወዳጄ በጉዳዩ ላይ ለሰዓት በመንገድ እያዘገምን ንፁህ አየር እየተቀበልን ስንወያይ ብዙ አማራጭ መፍትሔዎቻችንና የሚያመጡ ውጤቶችን ላይ ተወያየን፡፡ በአንድም በሌላ መልኩ እንዴት ጉዳዩን መያዝ እንዳለበት ተወያየን፡፡ አብረን የተነጋገርን እያለ ድንገት ጥበብን የተሞላ መፍትሔ በሁኔታው ላይ በልቡ ሞልቶ በአፌ ላይ ሲመጣ ነገሩ የእግዚአብሔር እንደሆነ አውቃለሁ፡፡ ከአእምሮየየ የመጣ አይደለም፡፡ ከመንፈስ ከውስጠኛው ማንነት ነው የመጣው፡፡

እኔ የወሰንኩት ውሳኔ እንደማንኛውም ነገር በተፈጥሮአዊ ፍላጎት ለማድረግ አይደለም የወሰንኩት፡፡ አብዛናው የእኔ ትግል የተመሠረተው በሁኔታዬ የተመሠረተ ውሳኔዎችን እግዚአብሔር እንዲያጸድቅልኝ በማሳመን ላይ ነበር፡፡ የእግዚአብሔር ድምፅ ለእኔ ጭንቅ ነበር፡፡ ምክንያቱም እኔ ቀደም ብዬ በአእምሮዬ ከእርሱ ዕቅድ ውጭ የሆነን ነገር ወስኖአልና ነው፡፡ በአንድ ጉዳይ ላይ ችክ የሚል ሃሣበ ግትርነት የሠላም ጠላትና እግዚአብሔርን የመስማት አቅማችንን ይከልልብናል፡፡ እኛ ፈቃዳችንና ፍላጎታችንን በእርሱ ሥር ካላስገባን ከእርሱ ግልፅ የሆነ ቃል ወይ መመሪያ ሊያጣ እንችላለን፡፡ እሱ የሚሻለውን ጊዜ ያውቃል እኛ ለእርሱ ራሳችንን ለእርሱ ማስገዛት ሃሣባችንን ለሃሳቡ በማንኛውም ሁኔታ መታዘዝ አለብን፡፡

እግዚአብሔር ከፈለክነው ተስፋ ይሰጣል፡፡ እርሱ አፋችን መናገር በሚገባን ይሞላዋል፡፡ (መዝ 81÷ 10 ተመልከት) ይሄ ደግሞ እርሱ ለእኔ ያደረገ እውነታ ለአንተም ሊሰማው ከፈለክ የሚያደርግልህ ነውና እርሱን መፈለግና ለፈቃዱ ተገዥ ሁን፡፡


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- እግዚብሔር አፍህ እንዲሞላ ጠይቅ ዛሬ መናገር ያለብህን ቃል እንድሰጥህ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon