ኢየሱስ የመጣው ወደ ሰላም መንገድ ሊመራን ነው

ኢየሱስ የመጣው ወደ ሰላም መንገድ ሊመራን ነው

ይኸውም በጨለማ ለሚኖሩት፣በሞት ጥላ ውስጥም ላሉት እንዲያበራና ፣እግሮቻችንንም ወደ ሰላም መንገድ እንዲመራ ነው፡፡ – ሉቃ 1፡79

ሰላም እግዚአብሔር ከሰጠን ጥቅሞችና በረከቶች መሀከል በጣም አስፈላጊው ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ ነገር ግን ከየዕለት ተዕለት ጉዳዮቻችን እና ከሚያመጧቸው ጫናዎች የተነሳ ሰላም አይሰማንም፡፡ ነገር ግን እንደዛ መሆን የለበትም፡፡

ሉቃ 1፡79 ሲናገር እግዚአብሔር ኢየሱስን እንዲሰራው ከላካው ነገር አንዱ ወደ ሰላም መንገድ እንዲመራን ነው፡፡ ምንም ያህል ጊዜ የሌለን ሰዎችም ብንሆን እና በዙሪያችን ምንም ቢካሄድ እንደአማኞች በእግዚአብሔር ልዕለ ተፈጥሯዊ ሰላም ውስጥ የመራመድ ድንቅ እድል አለን፡፡

የመጀመሪያዎቹን የህይወቴን አርባ አመታት የኖርኩት ያለሰላም ነበር ፤ በመጥፎ ሁኔታ ውስጥም ነበርኩ፡፡ በመጨረሻ ሰላምን በጣም የተራብሁበት ነጥብ ላይ ከመድረሴ የተነሳ ሰላምን ለማግኘት አስፈላጊ የሆኑትን ለውጦች ሁሉ ለማምጣት ከእግዚአብሔር ጋር ለመስራት ፈቃደኛ ሆንሁ፡፡ ምስጋና ይግባውና አሁን አዕምሮን የሚያልፍ የሰላምን ህይወት በማጣጣም ላይ እገኛለሁ፡፡ አውሎ ነፋስ ሲኖር ብቻ ሳይሆን በህይወት አውሎነፋሳት መሀከልም ሁሉ በሰላም ጎዳና መጓዝ ችያለሁ፡፡

ሰላምን መከታተል ቅድሚያ ሰጥታችሁታል? እግዚአብሔር እንድትሰጡት ይፈልጋል፡፡ በክርስቶስ መብታችሁ ወደ ሆነው ሰላም መንፈስ ቅዱስን ተከተሉት፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ ወደ ሰላምህ እግሮቼን እንዲመራ እና እንዲያሳይ ኢየሱስን ስለላከው አመሰግናለሁ፡፡ በህይወቴ ትልቅ የሆነውን የሰላምህን በረከት ተቀብያለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon