እምነታችሁን ለመገንባት የመጀመሪያ ስልጠና

እምነታችሁን ለመገንባት የመጀመሪያ ስልጠና

ምክንያቱም የእምነታችሁ መፈተን ትዕግስትን እንደሚያስገኝ ታውቃላችሁ፡፡ – ያዕ 1፡3

ያደገ እምነት በአንድ ለሊት አይመጣም፡፡ በእግዚአብሔር ላይ ጥልቅ ፣ ጤናማ እና ጠንካራ እምነት እንዲኖረን ካስፈለገ ያድግ ዘንድ እምነታችንን መለማመድ አለብን፡፡

በውትድርና ውስጥ ያሉ ወታደሮችን አስቡ፡፡ በአንዱ የአገልግሎት ክፍል ውስጥ እንደተመደቡ ወዲያው በጣም ጠንካራ ለሆነው ጦርነት ዝግጁ አይደሉም፡፡ በመሰረታዊ ስልጠና ውስጥ ማለፍ አለባቸው፡፡ ያለእፍረት ልምምድ እና ስልጠና ያደርጋሉ፡፡ ይህንን የማብቃት ስራ የሚያከናውኑ አለማማጆች ይመደባሉ ምክንያቱም ወታደሮች ጥንካሬ ፣ ድፍረት ፣ በፍጥነት የማገገም አቅም እና ብርታት ያስፈልጋቸዋል፡፡

ይሄንን ነገር ከእምነታችን ጋር አያይዘን እንመልከተው፡፡ መጀመሪያ ህይወታችንን ለክርስቶስ አሳልፈን ሰጠን፡፡ ከዛ መሰረታዊ ስልጠናን ወይም እምነታችንን መገንባት ጀመርን፡፡ በእኛ ሁኔታ እንደ አሰልጣኛችን የሚሆነው መንፈስ ቅዱስ ነው፡፡

በጊዜውም ያለጊዜውም የተዘጋጀን እንድንሆን እያንዳንዳችን እምነት ለመገንባት የሚያስፈልጉንን መሰረታዊ ነገሮች ያውቃል፡፡ እምነታችንን እንዴት መገንባት እንዳለበት ያውቃል ብለን ማመን በከበደንም ጊዜ ቢሆን  የሚያስፈልገን መታዘዝ ብቻ ነው፡፡

መንፈስ ቅዱስ እንዲያሰለጥናችሁ ስትፈቅዱለት ውጤቱ-በእግዚአብሔር ላይ ጠንካራ እና ደልዳላ እምነት-ነው ለዚህም የሚፈጀው ጊዜ እና ጥረት ይገባዋል!


የጸሎት መጀመሪያ

መንፈስ ቅዱስ ራሴን ለአንተ ምሪት አስገዛለሁ፡፡ በአንተ ጠንካራ እና ያደገ እምነት እንዲኖረኝ እፈልጋለሁ፡፡በሁሉም ሁኔታ እና በሚያስፈልገኝ በሁሉም አቅራቦት እግዚአብሔርን በማመን በእምነት እንጂ በማየት እንዳልራመድ አሰልጥነኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon