እራስዎን የመሆን ድፍረት

ቃሉን በማመሰግነዉ አምላክ፣ በእግዚአብሔር ታምኜአለሁ፤ አልፈራም፤ ሥጋ ለባሽ ምን ሊያደርገኝ ይችላል? – መዝ 564

ጨዋታ መጫወት ፣ እርስን መደበቅ ወይም ሌላን ሰዉ ለመምሰል አድክሞሃል? ምን ወይም ማን መሆን እንዳለብህ ጫና ሳይኖርብህ ስለአንተነትህ ብቻ ተቀባይነትን የማግኘት ነጻነት አትፈልግም? ያንተን ልዩ ገጽታ ለማንጸባረቅና ሌሎችን እንድትመስል የሚደረገዉን ጫና እንዴት መቋቋም እንደምትችል መማር ትፈልጋለህ?

ዋስትና የማጣትን ስሜት ለማሸነፍና እግዚአብሔር እንድትሆን የጠራህን ሰዉ ለመሆን ከፈለግህ ልዩ የመሆንን ድፈረት ማግኘት አለብህ፡፡ ደስታማጣትና ፍርሃት የሚከሰተዉ የራሳችንን ልዩ ባህሪይ ስንቃዎምና ሌሎችን ለመምሰል ስንጥር ነዉ፡፡

በሌሎች ግምትና እንድትሆን በሚፈልጉት መንገድ ከመኖር ይልቅ እግዚአብሔብሔር አድርጎ የፈጠረህን ማንነት እድትወድና እንድትቀበል ይፈልጋል። ራስህን እንዲህ መጠየቅ አለብህ “እኔ እግዚአብሔርን ነዉ ወይስ ሰዎችን ነዉ ማስደስተዉ?” በህይወታችን እዉነተኛ ሰላምና ደስታ የሚመጣዉ ሰዎችን ሳይሆን እግዚአብሔርን በማስደሰት ስናተኩር ነዉ፡፡

እግዚአብሔር አንተን ሲሰራ ምን እያደረገ እንደሆነ ያዉቅ ነበር፡፡ አንተ ያለፍርሃትና በአስደናቂነት በእግዚአብሔር የተፈጠርክ ልዩ ሰዉ ነህ፡፡ በክርስቶስ አዲስ ፍጥረት እንደሆንክና በእርሱ ዋስትና እንዳለህ ተቀበል እርሱ እንድትሆን የፈለገዉንም ፈልግ፡፡

የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ! ሰዉን አልፈራም፡፡ ከአንተ ጋር ባለኝ ህብረት መተማመንና መደገፍ እፈልጋለሁ፡፡ ዛሬ አንተን ለማስደሰትና እንድሆን የፈጠርከዉን ሰዉ ለመሆን እደፋፈራለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon