እርሱን እየሰማኸው ነው?

እርሱን እየሰማኸው ነው?

«ስለ እርሱም የምንናገረው ብዙ ነገር አለን፥ ጆሮቻችሁም ስለ ፈዘዙ በቃል ልንተረጕመው ጭንቅ ነው» (ዕብ.5፡11)።

በህይወትህ ጥያቄዎችን ጠይቆህ ነገር ግን መልሱን መስማት ወይም ምናልባትም ለራሳቸው ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት ጊዜ ሰጥተው የማይሰሙ ሰዎች አጋጥመውህ ያውቃል? ከእንደዚህ ዓይነት ሰዎች ጋር፣ ከማይሰሙህ ጋር መነጋገር ከባድ ነው። አግዚአብሔር በዚህ ዓይነት አስተሳሰብ ለሰዎች ለመናገር ጥረት ለማድረግ አይቸግረውም። እርሱን የሚናገረውን ለመስማት ፈቃደኛ ካልሆንን እርሱ ለመስማት ፈቃደኛ የሆኑትን (የሚጓጉትን) ይፈልጋል።

ዕብ. 5።11 የተሟሉ በቂ የህይወትን መርሆችን እርሱን ለመስማት በማይፈልግ አስተሳሰብ (አመለካከት) ሳንጠቀም ጎድለን እንዳንገኝ ያስጠነቅቀናል። ለመስማት የመቅረብ አመለካከት ከመንፈሳዊ ድነቁርና ይጠብቀናል። ለመስማት የመቅረብ አመለካከት ያለው ሰው በችግር ውስጥ በሚገባበት ጊዜና የእግዚአብሔርን እርዳታ በሚፈልግበት ጊዜ ከእርሱ ለመስማት የሚፈልግ ብቻ ሳይሆን ነገር ግን በእያንዳንዱ የህይወቱ ገጽታዎች ሁሉ ከእርሱ ለመስማት የሚፈልግ ነው።

አንድ ሰው አንድ ነገር እንዲናገር ከእርሱ የምንጠብቅ ከሆነ ለዚያ ሰው ትኩረታችንን በመስጠት እርሱውም እርሷ የምትናገረውን ለመስማት እንዘጋጃለን። ለእግዚአብሔርም ጋር ላለን ግንኙነትም እንደዚሁ ነው፤ ሁልጊዜ ከእርሱ ለመስማትና ድምጹን ለመስማት ሙሉ በሙሉ የተዘጋጀንና ከእርሱ ለመስማት የምንጠባበቅ ልንሆን ይገባናል።

ኢየሱስ ሰዎች ለመስማት ጆሮ አላቸው፣ ነገር ግን አይሰሙም፤ እንዲሁም ለማየት ዓይን አላቸው ነገር ግን አይመለከቱም (ማቴ. 13፡ 9 – 13)። እርሱ እየተናገረ የነበረው ስለ አካላዊ የመስማትና የማየት ብቃቶች አልነበረም፣ ነገር ግን ወደ እግዚአብሔር መንግስት ለመግባት ዳግም ስንወለድ ስለተቀበልነው ስለ መንፈሳዊ ጆሮና ዓይን ነበር የሚናገረው። መንፈሳዊ ጆሮአችን ከእግዚአብሔር ለመስማት የምንጠቀምበት ነው። እኛ ከእግዚአብሔር ለመስማት የታጠቅን ሰዎች ነን፣ ነገር ግን ማመን ያለብን ከእርሱ ለመስማት እንደምንችል ነው። ሁሉም የእግዚአብሔር ተስፋዎች በህይወታችን ገሃዳዊ ወይም ተጨባጭ የሚሆኑት በእምነት ነው። ስለዚህ ከእግዚአብሔር እንደምትሰማና መስማት እንደምትችል በማመን ዛሬውኑ ጀምር።


ዛሬ ለአንተ ያለው የእግዚአብሔር ቃል፡ መንፈሳዊ ጆሮህን ተጠቀም።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon