እርሱ ሁሉን በአንድላይ ይይዛል

እርሱም ከሁሉ በፊት ነው ሁሉም በእርሱ ተጋጥሞአል። – ቆላ 1:17

ላስይስ 1፡17 እጅግ ዉብ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ነዉ፡፡ ክፍሉ ኢየሱስ ሁሉንም ነገር በአንድ ላይ እንደያዘ ይነግረናል፡፡ ግሩም ነዉ! ይህንን የማያስተዉሉ ሰዎች እንኳን በእርሱ የተያዙ ናቸዉ፡፡

ስለዚህ ነገር አስብ፡፡ ኢየሱስ በአንድ ላይ ካልያዛቸዉ ጥሩ ትዳር ሊኖረን አይችልም፡፡ ኢየሱስ ግንኙነቶቻችንን እያሳደገዉ ካልሆነ ጥሩ ሰዉ ወደ መሆን አንሄድም፡፡ ኢየሱስ ከሌለበት ፋይናንሳችንም ቀዉስ ዉስጥ ሊገባ ይችላል፡፡ አእምሮአችንና ስሜታችን ኢየሱስ ከሌለበት አደጋ ሊገጥመዉ ይችላል፡፡ ያለ ኢየሱስ ሁሉም ነገር የተተራመሰ ነዉ፡፡

ኢየሱስ የህይወታችን እጅግ ጠቃሚዉ ነገር ካልሆነ ቅድሚያ የምንሰጣቸዉን ነገሮች እንደገና ማስተካከል አለብን፡፡ ማቴ 6፡33 አስቀድመን እግዚአብሔርንና መንግስቱን እንድንፈልግ ነዉ የሚነግረን ምክንያቱም ቀዳሚዉን ነገር ቀዳሚ ካለደረግን ሌላዉም ነገር ያለቦታዉ ይቀመጥና ህይወታችን ችግር ዉስጥ ይወድቃል፡፡ የእግዚአብሔርን መንግስት መፈለግ፣ መሆንና ማድረግ በእርሱ እይታ እርሱ ነገሮችን እንዴት እንድናደርግ እንደሚፈልግ፣ ሰዎችን እንዴት መያዝ እንደላብን፣ ሁኔታዎችን እንዴት ማስተዳደር እንዳለብን፣ ገንዘባችንን እንዴት ማዉጣት እንዳለብን፣ ምን ዓይነት አመለካከት መያዝ እንዳለብን እና ለእኛ ምን ዓይነት መዝናኛ ጥሩ እንደሆነ በእርሱ እይታ ማየት ነዉ፡፡

ዛሬ ለእርሱ በህይወትህ ቀዳሚዉን ስፍራ በመስጠት ጀምር፡፡ እርሱ አንድ ላይ ይይዛችኋል፣ እርሱን እንድትከተል ነዉ የፈጠረህ፤ እርሱን በህይወትህ ቀዳሚ አድርግ፡፡

የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ ያለ አንተ ምንም ነኝ፡፡ እኔን አንድ ላይ ይዘሀኛል እርግጥ ሁሉንም ነገር አንድ ላይ ይዘሀዋል፡፡ አንተ በህይወቴ እጅግ ጠቃሚዉ ነገር ነህ አንተን የህይወቴ ቁንጮ አደርጋለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon