ነገር ግን በእውነት የሚሰግዱ ለአብ በመንፈስና በእውነት የሚሰግዱበት ጊዜ ይመጣል፤ አሁንም ሆኗል፤ አብ ሊሰግዱለት እንደነዚህ ያሉትን ይሻልና፡፡ – ዮሐ 4፡23
አምልኮ መዝሙር ከመዘመር እጅግ የላቀ ነው፡፡ አምልኮ የልባችንን ዝናባሌና የአዕምሯችንን ሁኔታ ያመለክታል፡፡ ይህም ማለት ምንም መዝሙር መዘመር ሳያስፈልግ በፍቅር ስሜት ብቻ ማምለክ እንችላለን፡፡ ለእግዚአብሔር ያለን አምልኮ ውልደቱ ልባችን ነው፤ ይህ አምልኮ ሃሳባችንን ይሞላዋል፤ ከዚያም በምንናገረው ቃላትና በምንኖረው ኑሮ ይገለጣል፡፡
ዓለም አምልኮን ስታስብ ከመፅሐፍ ቅዱስ አምልኮ የማይገናኝ ልክ እንደ ሃይማኖታዊ ድርጊት ነው፡፡ አምልኮ ግን ከእግዚአብሔር ጋር የሚኖርን ግለሰባዊ ግንኙት እና ሰዎች ለእግዚአብሔር ካላቸው ከልብ የሆነ ፍቅር የተነሳ ምን ያህል የተሰጡ መሆናቸውን ማሳያ ነው፡፡ እውነተኛ አምልኮ ማለት ይህ ነው፡፡
‹በእውነትና በመንፈስ› የሚያመልኩ ሰዎችን እግዚአብሔር በብርቱ እንደሚፈልግ መፅሐፍ ቅዱስ ይነግረናል፡፡ ይህን እውነት በጣም አስደናቂ ሆኖ አግኝቼዋለሁ፤ ምክያቱም ማንም ሰው ተነስቶ እርሱን እንዲያመልክ አይፈልግም፡፡ የእርሱን እውነት ከልባቸው የሚኖሩ እውነተኛ የሆኑ ሰዎችን ይፈልጋል፡፡ ከግዴታ፣ ከሃይማኖት ወይም ከፍርሃት የመነጨ አምልኮ እንድናቀርብለት አይፈልግም፡፡
እውነተኛ አምልኮ የሚመነጨው ከእግዚአብሔር ጋር በሚኖረን የጠበቀ ወዳጅነት ነው፡፡ ዛሬ እግዚአብሔርን በሙሉ ልባችን እናምልከው፤ በተጨማሪም በእውነትና በመንፈስ አምላኪ ሁኑ፡፡
የጸሎት መጀመሪያ
ጌታ ሆይ! በከንፈሬ ብቻ ላመልክህ አልፈልግም፡፡ ከዚያ ይልቅ እንደእውነተኛ አምላኪ ህይወቴን ለአንተ መስጠት እፈልጋለሁ፣ ከአንተም ጋር በብርቱ መጣበቅ እፈልጋሉ፡፡አንተ ለእኔ እጅግ መልካም አምላክ ነህና ‹በእውነትና በመንፈስ› ላመልክህ እፈልጋለሁ፡፡