«…የተራበችን ነፍስ አጥግቦአልና፥ የተራቈተችንም ነፍስ በበረከት ሞልቶአልና»(መዝ.109፡7)።
ከእግዚአብሔር ጋር ካለህ የግል ልምምድ በህይወትህ ብዙ እርካታ እንዳገኘህ ተስፈ አደርጋለሁ። እርሱ ለምትናፍቀው ነፍስ እውነተኛ እርካታ ለመስጠት አንዱና ብቸኛው ነው። ስለዚህ በባዶና ምንም ሊያረኩህ በማይችሉ ነገሮች ጊዜህን አታባክነው።
አሁን በእጅህ ባሉ ነገሮች፣ በሄድክባቸው ሥፍራዎች ወይም ባደረግሃቸው ነገሮች ያለ እግዚአብሔር ምንም ዓይነት እርካታ ሊሰጡህ አይችሉም። ገንዘብ፣ ጉብኝት (ጉዞ)፣ መኖሪያ ቤትና የቤት ዕቃዎች፣ ልብሶች፣ ትልልቅ ዕድሎች፣ ትዳር፣ ልጆች፣ እናም ሌሎች ብዙ ዓይነት በረከቶች ለተወሰኑ ጊዜያት አስደናቂ የደስታ ምንጮች ሊሆኑ ይችላሉ። ነገር ግን ደስታህ መመሥረት ያለበት በተሰጠህ የዕድሜ ክልል ከውጪያዊ ሁኔታዎች ፈጽሞ በተለየና ራሱን የቻለ ሆኖ በውስጣዊ ዋስትናዎች ላይ የሆነ እውነተኛ ደስታ እንዲኖርህ እግዚአብሔር ይፈልጋል።
እግዚአብሔርን በህይወታችን ቀዳሚ ካላደረግነው በቀር ፈጽሞ በቋሚነት እርካታ ያገኘን ልንሆን አንችልም። እናም ይህንን ስናደርግ እርሱ ደግሞ የሚያስፈልጉንን ነገሮች ሁሉ ይጨምርልናል (ማቴ. 6፡33 ይመልከቱ)። እኛ አካላዊ ሥጋችንን ለመመገብ ጊዜን፣ ገንዘብንና ጥንቃቄን አድርገን በእያንዳንዱ ቀናት አስፈላጊውን ምግብ እንመግበዋለን። አንዳንድ ጊዜ እንዲያውም በቀጣይ ቀናት የምንበላውን ምግብ ጭምር አስቀድመን ልናውቅ እንችላለን። ተፈጥሮአዊ አካላችንን እንደምንመግበው ሁሉ መንፈሳዊ ህይወታችንንም መመገብ ይገባናል። ብዙውን ጊዜ ቃሉን ሳንመገብና በእርሱ ህልውና ሳንሞላ ከእግዚአብሔር ጋር የጠበቀ ህብረት አለን ብለን የምናስብ ይመስላል። ለአካላዊ ሥጋችን ምግብ እንደሚያስፈልገው ሁሉ ቢያንስ እርሱን በትጋት መፈለግ ይኖርብናል።
የተፈጠርነው ከእግዚአብሔር ጋር ወሳኝና ህያው ህብረት አድርገን እንድንደሰት ነበር። እናም ሁልጊዜ አንድ ነገር እስካላስደሰተን ድረስ ብዙ ጊዜ ይህንን ዓይነት ህብረት ቸል እንለዋለን። በእግዚአብሔር ቃል ለመደሰትና በየቀኑ በህልውና ውስጥ በመሆን ጊዜ ከወስደን በህይወታችን ጥልቅና ቀጣይነት ያለውን እርካታ እንለማመዳለን።
ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- አካላዊ ሥጋህን እንደምትመግበው ነፍስህንም መግብ።