እውነተኛ ፍቅር መስጠት አለበት

እውነተኛ ፍቅር መስጠት አለበት

ፍቅር ይህ ነው፤እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው ሳይሆን እርሱ እንደ ወደደንና ስለ ኀጢያታችን ማስተሰረያ ይሆን ዘንድ ልጁን መላኩ ነው፡፡ወዳጆች ሆይ እግዚአብሔር እንዲህ ከወደደን፣እኛም እርስ በእርሳችን መዋደድ ይገባናል፡፡ – 1 ኛ ዮሐ 4፡10-11

ሁሉም ሰው መወደድንና ተቀባይነት ማግኘትን ይፈልጋል፡፡ነገር ግን ብዙዎቻችን ደስታን ለማግኘት የምንፈልገው በተሳሳተ መንገድ ነው፡፡በመቀበል ውስጥ ልናገኘው እንሞክራለን ነገር ግን የሚገኘው በመስጠት ውስጥ ነው፡፡የእግዚአብሔር ፍቅር ከተሰጠን ስጦታ በጣም ውዱ ነው፡፡አንዴ ወደ እኛ ከፈሰሰ በኋላ ከእኛ ወደ ሌሎች ደግሞ መፍሰስ አለበት ያለበለዚያ አንድ ቦታ ይረጋል፡፡

ፍቅር መስጠት አለበት ምክንያቱም ተፈጥሮው ነው፡፡አንደኛ ዮሐ.4፡11 የተቀበልነውን ፍቅር መስጠት እንዳለብን አጉልቶ ያሳያል፡ወዳጆች ሆይ እግዚአብሔር እንዲህ ከወደደን፣እኛም እርስ በእርሳችን መዋደድ ይገባናል፡፡

በእግዚአብሔር እውነተኛ ፍቅር ውስጥ መኖር ሂደት ነው፡፡መጀመሪያ እርሱ ወደደን እኛም በእምነት ፍቅሩን ተቀበልን፡፡ከዛ እኛ ራሳችንን ሚዛናዊ በሆነ መንገድ እንወዳለን፡፡ለእግዚአብሔር ፍቅር መልሰን መስጠትና ሌሎች መውደድ እንማራለን፡፡

ፍቅር ይሄንን አካሄድ መከተል አለበት ወይም ያልተሟላ ፍቅር ነው፡፡የእግዚአብሔር ፍቅር አንዴ በውስጣችን ከገባ በኋላ ልናካፍለው እንችላለን፡፡ሌሎችን በደንብ መውደድን ልንመርጥ እንችላለን፡፡እግዚአብሔር እንደሚወደን ያለ ምክንያት እና በጥልቀት ልንወዳቸው እንችላለን፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

ጌታ ሆይ ፍቅርህ በውስጤ ረግቶ እንዲቀመጥ አልፈልግም፡፡ፍቅርህን ተቀባይ ብቻ ሳልሆን ሌሎችንም መውደድን በመምረጥ ሂደቱን ሙሉ እንዳደርገው እርዳኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon