እያንዳንዱን ሰው በተለያየ መንገድ ውደዱ

እያንዳንዱን ሰው በተለያየ መንገድ ውደዱ

ግሩምና ድንቅ ሆኜ ተፈጥሬያለሁና አመሰግንሀለሁ፤ስራህ ግሩም ነው፣ ነፍሴም ይህን በውል ተረድታለች፡፡ – መዝ 139፡14

መጽሀፍ ቅዱስ ሲናገር ግሩም እና ድንቅ ሆነን ተፈጥረናል ይላል፡፡በእያንዳንዳችን ላይ እግዚአብሔር ጊዜ ወስዶ የፈጠራ አቅሙን ተጠቅሟል፡፡ስለዚህ እያንዳንዳችንን አንድ አይነት አድርጎ ላለመፍጠሩ ምክንያት አለው፡፡አይደለም?

እንዳለመታደል ሆኖ አንዳንዴ ሁሉንም ሰዎችንአንድ አይነት እንደሆኑ አድርገን ለመውደድ እንሞክራለን፡፡

ከዛ ሁሉም ሰዎች ከእናንተ ተመሳሳይን ነገር እንደማይፈልጉ ትረዳላችሁ፡፡ አንዱ ልጃችሁ ለምሳሌ ከሌላው ይልቅ ከእናንተ ጋር በግል ጊዜ ማሳለፍ ከሌሎቹ አብልጦ ሊፈልግ ይችላል፡፡አንዱ ጓደኛችሁ ከሌላው በላይ በቋሚነት ማበረታታትን ሊፈልግ ይችላል፡፡አንዳንድ ሰዎች በቃ የተለያዩ የፍቅር አይነቶችን ይፈልጋሉ፡፡

የእያንዳንዱን ሰው ምርጫ እና አስተያየትን ማክበር ሌላው በጣም አስፈላጊ ነገር ነው፡፡ራስ ወዳድ ሰዎች ሰው ሁሉ እንደነርሱ እንዲሆን ነው የሚፈልጉት፥ ፍቅር ግን በሰዎች መሃል ያለውን ልዩነት ያከብራል፡፡እግዚአብሔር ሁላችንም አንድ አይነት እንድንሆን ቢፈልግ ኖሮ ለእያንዳንዳችን የተለያየን የእጅ አሻራ አይሰጠንም ነበር፡፡ይሄ እውነታ ብቻ ሁላችንም እኩል ግን የተለያየን ሆነን እንደተፈጠርን ያረጋግጣል ብዬ አምናለሁ፡፡

እኛ ሁላችን የተለያዩ ስጦታዎች እና መክሊቶች፣የተለያዩ የምንወዳቸው እና የማንወዳቸው ነገሮች፣የተለያዩ የህይወት ግቦችና  የተለያዩ የውስጥ ፍላጎቶች አሉን፡፡ሰውን የሚወድ ሰው በሌሎች ውስጥ ያለውን ልዩነት አክብሮ ያበረታታል፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ በሌሎች ውስጥ ያለውን ልዩነት እንዳደንቅ እና እንደሁኔታቸው እንድወዳቸው እርዳኝ፡፡ሁላችንም ግሩም እና ድንቅ ሆነን ነው የተፈጠርነው፡፡ወደ ህይወቴ ስለላካቸው ሰዎች ድንቅ አፈጣጠር አመሰግንሀለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon