አባ አባት ብለን የምንጮኽበት የልጅነት መንፈስ ጸቀበላችሁ እንጂ እንደገና ለፍርሃት የባርነትን መንፈስ አልተቀበላችሁምና፡፡ – ሮሜ 8፡15
ፍርሃት በሕይወታችን ላይ ከባድ ተጽዕኖ ሊሆን ይችላል ይሁን እንጂ ጠላት የእምነታቸንን አቅጣጫ የሚያስትበት ነው፡፡ ጸሎታቹ የማይጠቅም ነው ፤ ከእግዚዘብሔር ፊት ለመቆም አትበቁም ፤ ወዳቂዎች ናችሁ፤ ፍርሃት እኔ የምላችሁን እመኑ ነው የሚለን፡፡
ፍርሃት ያልሆናችሁት ፣ የሌላችሁን የማትችሉትን እና ፈጽሞ ሊኖረችሁ የማይችል ነገር ነው የሚናገረው፡፡ ነገር ግን ሮሜ 8፡15 ‹‹አባ አባት ›› በማለት ልትጠሩት የምትችሉ የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችሁን ይናገራል፡፡
አባ የሚለው ቃል ትናንሽ ልጆች አባታቸውን የሚጠሩበት ቃል ነው፡፡ አባት ከሚለው ቃል በመጠኑ ከመደበኛ መጠሪያነት ይለያል ፤ ምቹ የሆነ ቀረቤታ በአባት እና በልጁ መካከል እንዳለ ይጠቁማል፡፡
ኢየሱስ እግዚአብሔርን አባ ብለን መጥራት እንችላለን ብሎናል፡፡ ምክንያቱም ከፍርሃት ቀንበር ነጻ አውጥቶናል፡፡ ያለምንም ዓይነት ፍርሃት ወደ እርሱ ብንቀርብ እርሱ ልጆቹን ዘወትር ይንከባከባል፡፡ ችግሮቻችንን እና ህመማችንን ይዘን ወደ እርሱ ስንመጣ እጆቹን ከፍቶ ሊያጽናን እና ሊያበረታታን ይጠብቀናል፡፡
ጸሎት ማስጀመሪያ
አብ አባት ሆይ ልጅህ ስላደረከኝ አመስግንሃለሁ፡፡ እንደምትንከባከኝ አውቃለሁ ፤ በፍርሃ ቀንበር ውስጥም መኖር አልፈልግም፡፡ እወድሃለሁ።