እግዚአብሔርን “አንድ ነገርህ” አድርገዉ

እግዚአብሔርን “አንድ ነገርህ” አድርገዉ

እግዚአብሔርን አንዲት ነገር ለመንሁት እርስዋንም እሻለሁ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ፥ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘውንም አይ ዘንድ፥ መቅደሱንም እመለከት ዘንድ። – መዝ 27:4

ህይወት የተወሳሰበ መሆን የለበትም፡፡ ኢየሱስ የሞተዉ እኛ የተወሳሰበ፣ የሚያበሳጭ እና የተዘበራረቀ ህይወት እንድንኖር አይደለም፡፡ ዮሐ 10፡10 የሚናገረዉ እርሱ የሞተዉ ህይወት እንዲኖረንና እንድንደሰት እንደሆነ ነዉ፡፡ ነገሮች የሚወሳሰቡበት ደቂቃ ደስታችንን የሚሰርቅበት ደቂቃ ነዉ፡፡ በጭንቀት በተሞላና በጣም ስራ የሚበዛበት የህይወት ዘይቤ መኖርን ማቆም አለብን፡፡

የዚህ ተቃራኒ የህይወት ዘይቤ ደግሞ ቀለል ያለ ነዉ፡፡ ቀላል ሕይወት ማለት ነጠላ፣ ቋሚና ያልተወሳሰበ ህይወት መኖር ማለት ነዉ፡፡ ቀላል ህይወት ስለመኖር እግዚአብሔር ከእኔ ጋር አዉርቶ ያዉቃል፡፡ ይህንን የማድረጊያዉ ብቸኛዉ መንገድ “ለአንድ ነገር” መኖር ነዉ፡፡

እግዚአብሔር ስለ እርሱ እንድንሆን ይፈልጋል፡፡ ወደ እርሱ እንደ ህጻናት ሆንና አምናለሁ እያልን ካልመጣን የእርሱን መንግስት እንደማንወርስ ተናግሯል፡፡

ይህ እጅግ ቀላል ይመስላል እና ማወሳሰብ ልትፈልግ ትችላለህ ነገር ግን እንዳታደርገዉ! እግዚአብሔር ለአንተ ያለዉ ዓላማ ቀላል ነዉ፡፡ ይህ ለአእምሮህ ምንም ትርጉም አይሰጥ ይሆናል ነገር ግን እግዚአብሔር ምንም የተወሳሰበ ነገር የለዉም እርሱም የተወሳሰብክ እንድትሆን አይፈልግም፡፡ ዛሬ ወደ እርሱ ቀርበህ እንዲህ በል “አምናለሁ” እርሱን “አንድ ነገርህ” አድርገዉ፡


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ! በአንተ አምናለሁ፡፡ በማወሳሰቤ ጫና የበዛበት ህይወት መኖር አልፈልግም ስለዚህ ዛሬ አንተን አንድ ነገር በማድረግ ቀላል ህይወት እፈልጋለሁ ለእኔ ባለህ ቀላል ዕቅድ ምራኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon