እግዚአብሔር ለእናንተ ያለው እቅድ መታመን መማር

እግዚአብሔር ለእናንተ ያለው እቅድ መታመን መማር

መንገድህን ለእግዚአብሔር ዐደራ ስጥ፤ በእርሱ ታመን፤ እርሱም ያከናውንልሃል፤ – መዝሙር 37፡5

በእግዚአብሔር መታመንን በመማር ሕይወትህን በቀለላሉ መምራት ትችላለህ፡፡ ብዙ ጊዜ በእዚአብሔር ለመታመን አንፈቅድም፡፡ ምናልባት ከዚህ በፊት ብዙ ጊዜ ተከድተህ ይሆናል ወይም ደግሞ በራስህ የምትደገፍ ሰው ትሆናለህ፡፡ ያም ቢሆን በእግዚብሔር መደገፈን ልትማር ይገባል፡፡

ሕይወታችንን ለማቅናት በቀላሉ ልንጨነቅ እና ልንሯሯጥ እንሞክራለን ነገር ግን ሙከራችን አይሳካም፡፡ በእግዚብሔር የሚታመን ሰው መንገዱ ምርጥ እንደሆነ ያውቃል፡፡ መታመን በቅጽበት የሚከሰት ምትሃት አይደለም፡፡ መታመን የእምነት እርምጃዎችን በመውሰድ እና የእግዚአብሔርን ታማኝነት በመለማመድ የሚያድግ ነው፡፡

ምልዑ በሆነ አግባብ በእግዚአብሔር በመታመን የምትኖር ከሆነ ፍርሃትን ፣ አለመረጋጋትን ምናልባትም በራስ መደገፍን መቃመወም አለብህ፡፡ ይህን የምታደርግ ከሆነ በኑሮህ ትግል ውስጥ አትገባም፡፡

በእግዚብሔር መታመን ለነፍሳችን ልዕለ ተፈጥሯዊ ረፍትን ያጎናጽፋል ፤ እርሱ በሚፈልገው መንገድ በነጻ እና በቀላሉ መኖር ትለማመዳለህ፡፡ በማይመስል ሁኔታ ውስጥ እንኳን በእግዚአብሔር መታመን እና በእርሱ የሚገኘውን ነጻነት እና እረፈት መለማመድ ይገባል፡፡


ጸሎት ማስጀመሪያ

እግዚብሔር ሆይ ያንተ መንገድ ከእኔ ይልቃል፡፡ በራሴ ብርታት መደገፍ የትም አያደርሰኝም፡፡ አቤቱ በአንተ እታመናለሁ፡፡ ለእኔ ባይመስለኝም እንኳን በአንተ እታመናለሁ፡፡ ፈቃድህ በሕይወቴ እንሚሆን አውቃለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon