እግዚአብሔር ለጥያቄዎችህ ሁሉ መልስ አለዉ

እግዚአብሔር ለጥያቄዎችህ ሁሉ መልስ አለዉ

በመከራ ቀን እግዚአብሔር ይስማህ፤ የያዕቆብ አምላክ ስም ያቁምህ። (መዝ 20፡1)

መልካም ግንኙነት እሰካሁን ለማድረግ ሞክረህካልቻልክ፤ ገንዘብህን በሚገባ ለማስተዳደር ካልቻልክ፤ ስራ እንዲኖርህሞክረህካልቻልክ፤ በንፈሳዊ ህይወት ለማደግ ሞክረህካልቻልክ፤ ችግር ዉስጥ ገብተሃል ማለት ነዉ፡፡

ችግሮች የህይወታችን አካል ስለሆኑ አንዱን ችግር ስናስወግድ ምናልባትም ወዲያዉኑ ሌላ ችግር ከኋላዉ ሊገጥመን ይችላል! ምንም እንኳ በድል ህይወት ብንመላለስም ችግሮችን ለመጋፈጥ የበሰለ ችሎታ ፅናትና ጥንካሬቢኖረንም ሁሉንም ለመቋቋም አቅም ያለን ሰዎችብንሆንም እዉነታዉ ግንሁላችንም ሁል ጊዜ
ካንዱ ወይም ከሌላዉ ችግርጋር መታገላችን የማይቀር ሃቅ ነዉ፡፡

በህይወታችን ለሚገጥሙን ችግሮች እግዚአብሔር ብቻ መፍትሄ ስላለዉ ለሱ አሳልፎ መስጠት የተሻለ ነገር ነዉ፡፡ ስለችግሮቹከማሰላሰል፣ከማዉራትናከመጨነቅ ይልቅ እግዚአብሔር እዲሰራ አሳልፎ መስጠት ይኖርብናል፡፡ ጭንቀቶቻችንን ሁኔታዎቻችንና ለእግዚአብሔር አሳልፎ መስጠትን እየተለማመድን በመጣን ቁጥር በህይወታችን የበለጠ ደስተኞችና መልካም ሰዎች አየሆንን እንሄዳለን፡፡

እኛ በህይወታችን ዘመን ሁሉ የተመኘነዉንና የታገልንበትን ነገር እግዚአብሔር ግንወዲያዉ በአንድ ጊዜናበተሻለ ምንገድ ሊሰራዉ ይችላል፡፡ ሳይዘገይም ሊናገርህና ነገሮችህንም ወዲያዉ ሊቀይር ይችላል፡

፡ ከእሱ የሚወጣዉ አንድ ቃል ለሁሉም መፍተሄ መሆን ይችላል፡፡ እግዚአብሔርን የሚያቅተዉ ትልቅ ነገር ወይም የሚያሳስበዉ ትንሽ ነገር አንዳች ነገር የለም፡፡ አናንተን ስለሚያሳስበዉ ነገር ሁሉ ይገደዋል ስለዚህ ችግሮቻችሁን ለእሱ አሳልፋችሁ ስጡና የሚያስፈልጋችሁን መፍትሄ እሱ እነዲያመጣ ፍቀዱለት፡፡


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡ ችግሮቻችሁን ለእግዚአብሔር አሳልፋችሁ ስጡና የሚያስፈልጋችሁን መፍትሄ እሱ እንዲያመጣ ፍቀዱለት፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon