እግዚአብሔር ሊያስተካክለን ይናገራል

እግዚአብሔር ሊያስተካክለን ይናገራል

ጌታ የሚወደውን ይቀጣልና የሚቀበለውን ልጅ ሁሉ ይገርፈዋል፡፡ ዕብ. 12÷6

እኛ ሁላችን በጊዜ መስተካከል ይኖርብናል፡፡ እንዲሁም የእግዚአብሔር ፍላጎት እኛን መናገርና እርሱ በእራሱ እኛን ማስተካከል ያለቀድሞና እኛ በእርሱ የመስተካከል እድልን ካልተጠቀምን፡- በኋላ በሌሎች ሰዎችና በሌላ ሁኔታዎች ተጠቅሞ ያስተካክለናል፡፡ ማስተካከያ ካሉት ከባድ ባሕሪያት ውስጥ አንዱ ለመቀበል በጣም የሚያስቸግር ሲሆን ይልቁን ደግሞ በሌሎች ሰዎች በኩል ሲመጣ በጣም ይከብዳል፡፡ ለዚህም እግዚአብሔር በመጀመሪያ በራሱ ረድቶን ሊያስተካክለን በጉዳያችን ጣልቃ ይገባል፡፡ ነገር ግን እርሱ ሊያስተካክን እንዴት እንደፈለገ ተረድተን እራሳችንን ለእርሱ ካልሰጠንና በራሱ ካላስተካከለን ምናልባት በአደባባይ በሌሎች ሊያስተካክለን ይችላል፡፡

አንድ ወቅት በውጭ ሀገር እያገለገልን ሳለን በምሣ ወቅት በምግብ ቤት ውስጥ አስተናጋጁ የሚመገበውን ከምግብ ዝርዝር (ሜኑ) እያሳየሁት ሳለ አስተናጋጁ ብዙም የእንግሊዝኛ ቋንቋ መናገር ስለማይችል መደናገጥ እና መደናገር በመካከላችን ተፈጠረ እኔ ደግሞ ፈፅሞ የእርሱን ቋንቋ መናገር ስለማልችል በፊቴ ላይና በድምፅ ላይ በምግብ ቤቱ ባሉ ሰዎች ሁሉ ፊት ይታይ ነበር፣ ምንም እንኳ ምሳሌው ለአገልግሎቴ ትምህርት ጥሩ አጋጣሚ ቢሆንም፡፡

አውቃለሁ ጥሩ ያልሆነ ባሕሪ አሳይቻለሁ፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር እንዲረዳው የፈለገው ነገር አለ፣ እኔና ባለቤቴ ዴቭ ወደ ሆቴል መኝታ ክፍል ስንመለስ ነገሩን አንስቶ ስህተቶቼን በማስረዳት ነገረኝ፡፡ ምንም እንኳ እርሱ ትክክል እንደሆነ ባውቅም ቶሎ ለመቀበል ከብዶብኝ ነበር፡፡ ነገር ግን እንደተቀበለው ሰው ሆኜ አንገቴን በመነቅነቅና ፊቴን ብሩህ በማድረግ ልሰማው ሞከርኩ ከዚያም ነገሩ እግዚአብሔር እርሱን ተጠቅሞ የእኔን ባሕሪ በጣም ጠቃሚ ለማድረግ እንደፈለገ አስተዋልኩ፡፡ ይሁን እንጂ አሁንም እግዚአብሔር እኔን ለማስተካከል ሌሎች አማራጭ መንገዶች ምናልባትም በሚያሳፍርና ስሜትን በሚጎዳ መልኩ ሊያስተካክለን ይችላል፡፡

ለመፀለይ ጀምርና እግዚአብሔር የማስተካከያ እርምት ስልክልህ ለመቀበል እንዲያስችልህ ጠይቀው፡፡ ምክንያቱም እርሱ በሌሎች በኩል የምልክልህ እርምት ለአንተ መልካም ነው፡፡

ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- የእግዚአብሔርን የማስተካከያ እርምት እምቢ በማለት አትቋቋም፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon