ታዘው ቢያገለግሉት፣ቀሪ ዘመናቸውን በተድላ፣ዕድሜያቸውንም በእርካታ ይፈጽማሉ።(ኢዮብ 36፡11)
ዴቭ እና እኔ በመደበኛነት ስለ ብዙ ነገሮች ከእግዚአብሔር መስማት እንፈልጋለን። ሰዎችን፣ ሁኔታዎችን፣ እና ብዙ ክስተቶችን እና የተወሰኑ ሁኔታዎችን እንዴት መያዝ እንዳለብን ከእሱ መስማት እንፈልጋለን። የዘወትር ጸሎታችን “ስለዚህ ጉዳይ ምን ማድረግ አለብን? ስለዚያ ጉዳይ ምን ማድረግ አለብን?” የሚል ነው።
ዴቭ እና እኔ ቶሎ ማስተዋል እና በእግዚአብሔር የተመሩ ውሳኔዎችን ማድረግ ያለብን በየሳምንቱ መቶ ነገሮች የሚከሰቱ ይመስላል። ሰኞ እግዚአብሔርን ካልታዘዝን ሳምንታችን አርብ ቀን ትርምስ ውስጥ ሊገባ ይችላል። ስለሆነም፣ ባለመታዘዝ ውስጥ እንዳንኖር ቆርጠናል።
ብዙ ሰዎች እርሱ ምን እንዲያደርጉ እንደሚፈልግ በማሰብ በህይወታቸው የተለየ የእግዚአብሔር ፈቃድ ያሳስባቸዋል። ለምሳሌ፦ “ጌታ ሆይ ይህንን ሥራ ልጀምር ወይስ ሌላ ሥራ እንድጀምር ትፈልጋለህ? ይህንን እንዳደርግ ትፈልጋለህ ወይስ ያንን እንድሰራ ትፈልጋለህ?” እግዚአብሔር የምንናፍቀውን የተወሰነ ምሪት ሊሰጠን እንደሚፈልግ አምናለሁ፣ ነገር ግን በቃሉ ውስጥ የሚገኘውን የሕይወታችንን አጠቃላይ ፈቃዱን ስለ መታዘዛችን ማለትም ሁል ጊዜ በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ አመስጋኝ ስለመሆን፣ በፍጹም ስለአለማማረር- ሁል ጊዜ ስለመርካትን፣ የመንፈስን ፍሬ ስለማሳየት እና የበደሉንን ወይም ያሳዘኑንን ይቅር ስለማለት የበለጠ ይገደዋል።
በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ቀደም ሲል የሰጠንን መመሪያዎች ካልታዘዝን ስለ ቀጥተኛ ፈቃዱ ምን እንደሚል ለመስማት እንቸገራለን። እግዚአብሔርን በበለጠ እና በግልፅ ለመስማት እና በህይወትህ ፈቃዱን ለመከተል ስትሞክር፣ በቃሉ ውስጥ ሥር በመስደድ አጠቃላይ ፈቃዱን ለማወቅ እና ለመታዘዝ ቅድሚያ መስጠትህን አስታውስ። ከዚያም በቀጥታ ሲናገርህ በቀላሉ ልትሰማው ትችላለህ።
ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡ ምን ማድረግ እንዳለብህ የምታውቀውን ማድረግህን ቀጥል፤ ምን ማድረግ እንዳለብህ በማታውቅበት ጊዜ እግዚአብሔር ያሳይሃል።