እግዚአብሔር በተከፈቱና በተዘጉ የእድል በሮች ይናገራል

እግዚአብሔር በተከፈቱና በተዘጉ የእድል በሮች ይናገራል

የዳዊት መክፈቻ ያለው የሚከፍት የሚዘጋም የሌለ፣ የሚዘጋ፣ የሚከፈትም የሌለ ቅድስና እውነተኛ የሆነው እርሱ እንዲህ ይላል፡፡ ራዕ 3 7

አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔር እኛ ለማድረግ የፈለግነውን ነገር በሮችን በመክፈትና በመዝጋት ይናገራል፡፡ ጳውሎስና ስላስ ወደ ቢታኒያ ሄደው እዚያ ላሉት ሕዝብ ወንጌል ለመስበክ መከሩ፡፡ ነገር ግን የኢየሱስ መንፈስ እንዳያደርጉ ከለከላቸው፡፡ (የሐዋ 16 6-7 ተመልከት) ነገሩ እንዴት እንደተደረገ እርግጠኛውን ነገር አናውቅም፡፡ ወደ ግዛቱ ለመሄድ እንዲሞክሩ በእርግጥ መገመት አያቅትም ሆኖም ግን እግዚአብሔር ወደዚያ ከመግባት ጠበቃቸው፡፡

ዴቭ (ባለቤቴ) እና እኔ የተለማመድነው እግዚአብሔር በሮችን ይከፍትልናል፡፡ ያንን የዕድል በሮች ደግሞ ማንም መዘንጋት አይችልም፡፡ እንዲሁም ደግሞ በሮችን ይዘጋል፡፡ ማንም በቀላሉ የማይከፍተውን፡፡ እኔ እውነትነት የሌለውን ነገር ለማድረግ አስብ ይሆናል፡፡ ነገሩ ስህተት መሆኑ ሲረጋገጥ ከዚያ በኋላ በእግዚአብሔር ላይ በመደገፍ እርሱ ፍቃድ ያልሆነውን በሮች እንዲዘጋው በእግዚአብሔር እደገፋለሁ፡፡

በሕይወቴ ለዓመታት እኔ የምፈልገው ነገር እንዲሆን በመሞከር ነው ያሳለፍኩት ውጤቱ ግን ተስፋ መቁረጥና፣ ቅር መሰኘት ነበር፡፡ ከዚያ ወዲህ የእኔ ድርሻ በብዙ በጣም ሠላማዊና አስደሳች የሆነው እኔ የእራሴን ድርሻ በማድረብ በእግዚብሔር ላይ በቀላሉ በመታመን እርሱ ከእርሱ ዕቅድ ጋር የሚስማማውን በሮች እንዲከፍተውና የእርሱ ፈቃድና እቅድ ያልሆነውን አጥብቆ እንዲዘጋው ሕይወቴን እተውለታለሁ፡፡ እግዚአብሔር እንደሚወድህ በትክክለኛ ሰዓት ላይ ታረጋግጣለህ፡፡ እርሱ ትክክለኛውን በር ይከፍትልሃል፡፡


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- በሕይወትህ በአንተ በራስህ ለአንተ ለራስህ አንዳች ነገር እንዲከናወን አትሞክር እግዚአብሔር ለአንተ ትክክለኛውን በሮች በመክፈትና የስህተት በሮችን እንዲዘጋልህ እርሱን ታመነው

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon