እግዚአብሔር ነገሮች በትክክለኛው ጊዜ እንዲሆኑ ያደርጋል

እግዚአብሔር ነገሮች በትክክለኛው ጊዜ እንዲሆኑ ያደርጋል

ራእዩ ገና እስከ ተወሰነው ጊዜ ነው፥ ወደ ፍጻሜውም ይቸኵላል፥ እርሱም አይዋሽም፤ ቢዘገይም በእርግጥ ይመጣልና ታገሠው፤ እርሱ አይዘገይም። – ዕንባቆም 2፡3

በልብህ የምታስበው ነገር እውን እንዲሆን በመጠባበቅ ላይ ነህ? ህልምህ እውን ሆኖ ትመለከት ዘንድ ስለ ፍርሃትና ወደ ኋላ ከሚጎትቱህ ሌሎች ነገሮች ነጻ ለመውጣት እየጸለይህ ነው? ወዳጆችህና ቤተሰቦችህ እንዲድኑ በመጸለይና በመጠባበቅ ላይ ነህ? ለሃብት፣ ለሞገስ፣ ለደረጃ ዕድገት፣ ለክብርና በቃሉ ውስጥ ላሉ በረከቶች ሁሉ እግዚአብሔርን ታምነኸዋል?

የጸሎቶችህን መልሶች መጠበቅ አድክሞህ ይሆን? ተስፋ ቆርጠህ ከሆነ፣ እየተንከራተትህ ከሆነ፣ እግዚአብሔር ሆይ መቼ ነው የሚሆነው የምትል ከሆነ አንዳንድ ጊዜ የእግዚአብሔር ሰአት ሚስጥር እንደሆነ ማወቅ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ እግዚአብሔር ነገሮችን በእኛ የጊዜ ሰሌዳ አይሰራም፡፡ ይሁን እንጂ እርሱ አይዘገይም በማለት የእግዚአብሔር ቃል ተስፋ ሰጥቶናል፡፡

እግዚብሔር ነገሮች በትክክለኛው ጊዜ እንዲሆኑ ያደርጋል፡፡ የአንተ ስራ ነገሮች መቼ እንደሚሆኑ ማሰብ ሳይሆን የመጨረሻዋን መስመር እስክታልፍ ድረስ ተስፋ ሳይቆርጡ በእግዚአብሔር በረከት ለመኖር ትኩረት መስጠት ነው፡፡ እግዚአብሔርን የበለጠ በታመናችሁና ዓይናችሁን በእርሱ ላይ ባደረጋችሁ መጠን የተትረፈረፈ ሕይወት ይኖራችኋል፡፡ እግዚአብሔርን መታመን ሕይወትን ይሰጣል፡፡ እርሱን ማመን እረፍትን ያመጣል፡፡ ስለዚህ ነገሮችን በራስ ለመለወጥ ማሰባችሁን አቁሙና እግዚአብሔር በሕይወታችሁ እግዚአብሔር መሆን እንዲችል ፍቀዱለት፡፡


ጸሎት ማስጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ ምንም እንኳ የአንተን ጊዜ መጠበቅ አድካሚ ሆኖ ቢሰማኝ የአንተ ጊዜ ትክክለኛ ነው፡፡ በአንተ እንድታመን ፣ አንተ ለእኔ ባለህ ዕቅድ ያረፍኩ እንድሆን እርዳኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon