
…በእናንተ ውስጥ ያለው በአለም ካለው ይበልጣል፡፡ – 1 ኛ ዮሐ 4፡4
በህይወታችሁ ያጋጠማችሁ ነገር ምንም ሆነ ምን ወይም ወደፊት ምንም ቢመጣ የሚያስፈልጋችሁን እምነት እግዚአብሔር ሰጥቷችኋል፡፡ላይመስል ይችላል እናንተም ለማሸነፍ የሚያስፈልገው ነገር እንዳላችሁ ላይሰማችሁ ይችላል፡፡ነገር ግን በእግዚአብሔር ላይ ያለ እምነት የሚመሰረተው በሁኔታዎች እና በስሜት ላይ አይደለም፡፡
እራሳቸሁን ልክ እግዚአብሔር እንደሚያያችሁ ማየት ህይወታችሁን ከፍተኛ ድል ይመራዋል፡፡ነገር ግን እምነት ይፈልጋል፡፡
እግዚአብሔር እንደሚወዳችሁ እና እንደልጁ እንደሚያያችሁ መስማት ብቻ ሳይሆን ማመን አለባችሁ፡፡የህይወትን መከራ ለማሸነፍ እና ወደፊት ለመጓዝ እምነት ያስፈልጋል፡፡እምነትን እንዴት እንደምታወጡት ካላወቃችሁ ደግሞ ምንም አይጠቅማችሁም፡፡እንዲሰራ እምነታችሁን ማውጣት አለባችሁ፡፡
እምነትን የምናወጣው በቃላችን፣በድርጊታችን እና በጸሎት ነው፡፡እርምጃ መውሰድ የእኛ ስራ ነው፡፡
አንደኛ ዮሐንስ 4፡4 ክርስቲያኖች ብዙ ጊዜ የሚጠቅሱት ጥቅስ ነው፡፡በቤተ-ክርስቲያንም ሆነ ከንፈረንስ ላይ ይሄንን ጥቅስ ስጠቅስ ሁሉም ሰው በደስታ ያጨበጭባል፡፡ስንት ሰው ነው ግን የእውነት በእኛ ውስጥ ያለው በአለም ካለው ይበልጣል ብሎ የሚያምን?
እውነታው ግን በእናንተ ያለው የሚበልጥ እና የሚወዳችሁ መሆኑ ነው፡፡ስለዚህ ዛሬ እምነታችሁን አሳድጉና እግዚአብሔር በሚያያችሁ መንገድ እራሳችሁን ተመልከቱ። ጠላት እንድታዩ የሚፈልገውም ሆነ ሁኔታዎች የሚመስሉት ምንም እምነታችን በእኛ ውስጥ በሚኖረው በኩል ያሸንፋል!
የጸሎት መጀመሪያ
እግዚአብሔር ሆይ እንደምትወደኝ እና ለማሸነፍ የሚሆን ሀይል እንደሰጠኸኝ አምናለሁ፡፡ልጅህ እንደመሆኔ መጠን በሰጠኸኝ እምነት በእያንዳንዱ ቀን በአንተ በመታመንና በመንገዴ የሚመጣውን ሁሉ እንቅፋት በማሸነፍ እመላለሳለሁ፡፡