በእግዚአብሔር ደስ ይበልህ የልብህንም መሻት ይሰጥሃል፡፡ መዝ 37፡ 4
እግዚአብሔር ለእኛ ከሚናገርበት መንገዶች ውስጥ አንዱ በልባችን ላይ የሚያመጣው የተቀደሰ ፍላጎቶቻችን ሲሆን ያንን ፍላጎታችንን ለእኛ በመስጠት ደግሞ ፈቃድ መሆኑን ይገልፅልናል፡፡ በሕይወቴ የማልረሳው አንድ ጊዜ እቤት የሚዘጋጅ ‹ዘኩኒ ዳቦ› አማረኝ ነገር ግን ለመሥራት እውቀቱም ጊዜውም አልነበረኝም፡፡ ዝም ብዬ ጌታ ሆይ ጥቂት የዝኩኒ ዳቦ አስፈልጎኛል ብዬ ከፀለይኩ በኋላ ጉዳዩን ተመልሼ አስቦ አላወኩም፡፡ ከሳምንት በኋላ የሆነች ስለ እኔ ፍላጎት የማታውቅ ሴት የታሸገ ነገር አስረከበችን ስከፍተው የቤት የዝኩረ ዳቦ ሆነ አገኘሁት፡፡ እግዚአብሔር ለትንሹም ለትልቁም ጥያቄ መልስ በመስጠት ሊያስደስተን ስለሚፈልግ በሁሉም ማድነቅና ማመስገን አለብን፡፡ እግዚብሔር የጻድቅና ቅዱስ የሆነ ፍላጎት (መሻት) እንዲሰጠን መጠየቅ አለብን፡፡ እንደተለመደው ለተፈጥሮአዊ ነገሮች ፍላጎት አለን ለምሣሌ እንደ ገንዘብ፣ ስኬት፣ ጥሩ ቤት፣ ጥሩ ግንኙነት ነገር ግን ለመንፈሳዊ ነገሮችም ፍላጎት ሊኖረን ይገባል፡፡ እግዚአብሔርን ለማወቅ በቅርበትና በጥልቀት ለማወቅና ፍላጎት ሊኖረን ይገባል፡፡ የመንፈሳዊ ፍሬ የሆነውን ፍቅር፣ እግዚአብሔርን በሚያከብር መልኩ ማገልገል፣ ሁልጊዜ እግዚአብሔር መታዘዝ ወዘተ፡፡ እግዚአብሔር ሥጋዊ ምኞታችንን አስወግዶ የተቀደሰ ፍላጎት እንዲሰጠን መጠየቅ አለብን፡፡
እግዚአብሔር በሕይወታችን የሚያመጣውና የሚጨምረው ፍላጎት የእርሱን ጽድቅ፣ ሠላምና ደስታ ይሰጠናል፡፡ (ሮሜ 14፡17 ተመልከት) እነዚህም ከእግዚአብሔር ቃል ጋር አይፃረርም፡፡
ክፉ ፍላጎትና ትዕግሥትና መረጋጋት አሳጥቶን እንድቀበል ያደርገናል፡፡ ነገር ግን የተቀደሰ ፍላጎት የሚመጣው ከእግዚአብሔር ፈቃድና ከእግዚአብሔር መንገድ በሰዓት ውስጥ በእርጋታ ውስጥ ነው፡፡
ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- መሻትህን በእግዚአብሔር ፊት ኢኑር፡፡ በጉዳዩ ላይ ፀልይና እግዚአብሔር ፈቃድና ጊዜ ሲሆን እንዲሰጥህ ታመን፡፡