የእውነት መንፈስ (እውነት ሰጪው መንፈስ) በመጣ ጊዜ ወደ እውነት (ሙሉ፣ወጥ እውነት) ሁሉ ይመራችኋል፡፡ – ዮሐ 16፡13
ጥሩ መነሻ ነጥብ ይመስላል ነገር ግን ብዙ እግዚአብሔር በእውነት ለሰዎች ይናገራል ወይ ብለው የሚጠይቁ ብዙ ሰዎች አሉ ብዬ አምናለሁ፡፡እንደዚህ አስባችሁ ታውቃላችሁ? እግዚአብሔር ይናገረኝ ይሆን ብላችሁ ራሳችሁን ጠይቃችሁ ታውቃላችሁ? መልሱ አዎ መሆኑን ስታውቁ ያስደስታችኋል፡፡
የምድር ህይወቱ ወደ ፍጻሜ ሲቃረብ ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ በዮሐ 16፡12-13 ብዙ የምነግራችሁ ነበረኝ፤አሁን ግን ልትሸከሙት አትችሉም፡፡የእውነት መንፈስ (እውነት ሰጪው መንፈስ) በመጣ ጊዜ ወደ እውነት (ሙሉ፣ወጥ እውነት) ሁሉ ይመራችኋል፡፡አላቸው፡፡
ኢየሱስ እነዚህን ቃላት ሲናገር የነበረው ያለፉትን ሶስት አመታት አብረውት ላሳለፉት ሰዎች ነበር…ነገር ግን አሁንም ሊያስተምራቸው የሚፈልገው ሌላም ነገር ነበር፡፡ይሄ የሚያስገርም ነገር ነው ምክንያቱም ኢየሱስ ከእኔ ጋር በግል ለሶስት አመታት ቀንና ለሊት ካሳለፈ ማወቅ ያለብኝን ሁሉንም ነገር እማራለሁ ብዬ ነው የማስበው፡፡
ነገር ግን ኢየሱስ ሁሌም የሚለው ሌላ ነገር አለው ምክንያቱም ሁሌም እኛ በህይወታችን እሱ ሊመራን የሚፈልግባቸው አዳዲስ ሁኔታዎች ያጋጥሙናል፡፡ለዚህም ነው ምንም እንኳ በአካል በፊታችን ባይቆምም እግዚአብሔር ሲናገረን መስማት እንድንችል መንፈስ ቅዱስ የተሰጠን፡፡
በክርስቶስ በኩል እና በመንፈስ ቅዱስ ሀይል በየዕለቱ እግዚአብሔር ፊትለፊት ሊናገራችሁ ይፈልጋል፡፡ለእናንተ ወዳስቀመጣቸው መልካም ነገሮች ደረጃ በደረጃ ሊመራችሁ ይፈልጋል፡፡
አብ የመንፈሱን ስጦታ ለሚጠይቁት ሁሉ ይሰጣል (ሉቃ 11፡13) ፡፡እንደገና በርህራሄ እያንዳንዳችን በየቀኑ ከእግዚአብሔር መስማት እና በመንፈስ ቅዱስ መመራት እንችላለን ማለት እፈልጋለሁ፡፡እየሰማችሁ ነው?
የጸሎት መጀመሪያ
እግዚአብሔር ሆይ በመንፈስ ቅዱስ ለመመራት እጠይቃለሁ፡፡እየተናገርከኝ እንደሆነ በማመን የምትለውን ለማወቅ እፈልጋለሁ፡፡