እግዚአብሔር ድንገት ይናገራል

እግዚአብሔር ድንገት ይናገራል

ክብሬ ትዘምርልህ ዘንድ ዝምም እንዳትል ልቅሶዬን ለደስታ ለውጥልኝ፣ ማቄን ቀድደህ ደስታንም አስታጠቅኸኝ፡፡ መዝ 30÷11

አርብ እለት ጧት በ1976 በጣም በጭንቀትና በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ሆኜ ሁሉንም ነገር ለማከናወን እየሞከርኩ ቤተክርስቲያን ያዘዘችንና የእግዚአብሔር ሃሳብ ከእኔ የምፈልገውን ሁሉ እያደረኩ በውስጤ ምንም ነገር ሊሰማኝ አልቻለም፣ እንዲያውም ተስፋ አስቆረጠኝ፡፡ በሕይወቴ ለውጥ እንደሚያስፈልገኝ ይሰማኛል፡፡ ነገር ግን ምን ዓይነት ለውጥ እንደሆነ አላውቅም፡፡ እየፈለኩ እንደሆነ አውቃለሁ፣ ነገር ግን ምን እንደሚፈልግ ግልጽ አይደለም፡፡

በማለዳው ወደ እግዚአብሔር በመጮህ ወደፊት መቀጠል እንዳልቻልኩ እያሉ ያልኩትን አስታውሳለሁ፡፡ ‹‹እግዚአብሔር ሆይ እኔ የማላውቀው ነገር የሆነ አለ፣ ነገር ግን አንድ ችግር አለ›› ነው ያልኩት፡፡

ከዚያ በሚያስገርም ድምፅ በተለየ መልክ ስሜን ጠርቶ ስለትዕግስት ተናገረኝ፡፡ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ አንድ ነገር ስለ እኔ ሁኔታ ሊያደርግ እንዳለ ታወቀኝ፡፡ በጆሮዬ ጌታ ለመንፈስ ቅዱስ መገኘት ከዚህ በፊት ባልተለማመድኩት መንገድ ተሰማኝ፡፡ የተሰማኝን ስሜት በጥሩ ለግልፅ የሆነ ሰው የፍቅር ውሃ ያፈሰሰብኝን ያህል ተሰማኝ፡፡ ወዲውኑ እንግዳ የሆነ ሰላም፣ ደስታ፣ ፍቅር በውስጤ አርፌና ወደውጭ ከመፍሰሱ የተነሣ በዙሪያዬ ያሉ ሁሉ መልካ ለውጥ እንደሆነ አስተውሉ፡፡ ከዚያ በኋላ የሌሎች ፍቅር ከዚህ በፊት በተለየ አደረብኝ፡፡

ከዚያ ሲመሽ በአዲስ መንገድ ጅማሪ ላይ እንዳለው በማወቅ ወደ አልጋዬ ሄድኩ፡፡ አብዛኛውን ጊዜ እግዚአብሔር በዚህ መልኩ ይሠራል፡፡ እርሱ ይናገርና በድንገት በሕይወታችን ይንቀሳቀሳል፡፡ ሌላ ቀንን አትጠብቅ ምክንያቱም እግዚአብሔር ድንገት የጉብኝትህ ቀን ሊያደርግ ይችላልና፡፡

ዛሬ የእግዚብሔር ቃል ለአንተ፡- ዛሬ ምናልባት የጉብኝት ቀንህ ሊሆን ይችላል፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon