ከእናንተ ማንም ጥበብ ከጎደለው ሳይነቀፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን ለእርሱም ይሰጠዋል፡፡ ያዕ 1÷5
አንዱ ምክንያት የእግዚአብሔርን ድምፅ የምንሰማበት ምክንያት ኃይልን የተሞላ የእግዚአብሔር ጥበብ በሁኔታዎች ላይ ስለሚለቀቅ ይህም የእግዚአብሔር ሙሉ በሙሉ ነገሮችን ስለሚለውጥና ስለሚቀይር ነው፡፡ የእርሱ ጥበብ በሁኔታዎች ላይ ሲመጣ ውሳኔም ይሁን፣ ኅብረትም ይሆንን የገንዘብ ጥያቄ፣ ስለ ጤና ጉዳይ ስለ ሥራ ሙያ ይሁን፣ የግል ጉዳይ ስለምርጫ የሕይወትን ዘመን ላይ ተፅዕኖ ለዓመታት የሚያመጣ የውስጠኛውን ዕይታና አቅጣጫ አንተ ምናልባት ለአንድ ጊዜም አስበው የማታውቀውን ይሰጥሃል፡፡ የእግዚአብሔር ጥበብ ገንዘብን፣ ሰዓትን (ጊዜን) ኃይልን (ጉልበትን) እንዲሁም ሕይወትን እንድታድን ያደርጋል፡፡ በሕይወትህ የማትጠብቀውን የበረከት ውጤት ያመጣል በተናቀበትና በተወለድክበት ቦታ መልስ ለክብርና ለሞገስ ያቆምሃል፡፡ በሕዝቦች መካከል ያለውን መለያየት ይፈውሳል፡፡ ጠቅላላ ተሃድሶን ሙሉ በሙሉ ከጠፋና ከወደመ ነገር ላይ ያመጣል፡፡ የእግዚአብሔር ጥበብ በተፈጥሮ ካለህ ይልቅ በጣም ጥበበኛና ብልጥ አድርጎ ወደ አስደናቂ ነገሮች ይመራሃል፡፡
የዛሬው ጥቅስ የምለው እግዚአብሔር ጥበብን ይሰጠናል፣ ነገር ግን ጠበብ መሆን ማለት ምን ማለት ነው; የሚለው ነው መታወቅ ያለበት፡፡ በአጭሩ ለማስቀመጥ ጥበበኛ ሰዎች አሁን የሚወስኑት ውሳኔ ወደፊት ወይም በኋላ የሚያስደስት ውሳኔን ነው መወሰን የሚችሉት፡፡ ጥበብኛ ያልሆኑ ሰዎች ግን አብዛኛውን ጊዜ ለጊዜው አሁን የሚወስኑት ውሳኔ አስደሳችና አብዛኛውን ጊዜ እግዚአብሔርን ጥበብ ስለማይጠይቅ በስሜታቸው ተገፋፍተው በሚወስኑት ውሳኔ በመጨረሻ ውጤት ንዴት ፀፀት ይሆንባቸዋል፡፡ ጥበበኛ ሰዎች በተፃራራ ዞር ብለው ያለፈውን ተዓምርና ምሳሌ ካለፈው ሁኔታ በመነሳት የእግዚአብሔርን ፀጋና ምርት እርሱን በጠየቁና በፈለጉ እንዲሁም በተመለከተ ጊዜ ይረዱታል፡፡ ማመን በሚከብድ ደረጃ የእግዚአብሔርን በረከት በእግዚአብሔር ምክር ያገኙትን ልምምድና ተሞክሮ በመገንዘብ በእግዚአብሔር ምርት ውስጥ ያለውን ጥበበኛነት ያላገኘውን ፍሬያማነት ያደንቃሉ፡፡ እግዚአብሔርን እንደምትፈልግ ሁሉ የእርሱን ጥበብ ጠይቅ፡፡
ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- ዛሬ የምትወስነው ነገ ወይም ፍፃሜው የሚያስደስትህ ውሳ ይሁን፡፡