እግዚያብሔር የሚለውን በሉ

እግዚያብሔር የሚለውን በሉ

ይህ የሕግ መጽሐፍ ከአፍህ አይለይ፤ በውስጡ የተጻፈውን ሁሉ በጥንቃቄ እንድትፈጽመውም ቀንም ሆነ ሌት ከሐሳብህ አትለየው፤ ይህን ካደረግህ ያሰብኸው ይቃናል፤ ይሳካልም፤ – ኢያሱ 1፡8

እግዚያብሔር እንደተናገረው በቃሉን በማጥናትና በማሰላሰል በጣም ብዙ ሰዓት ባሳለፍን ቁጥር እጅግ በጣም ብዙ በረከትና ከርሱ ጋር ቁርኝት ያለው ህብረት መገንባት እንደምንችል ነግሮናል፡፡ ከዚህም አልፎ እንደሚያበለፅገንና ስኬታሞች እንደሚያደርገን ይናገራል(ኢያ 1፡8)

ይህንን እኔ ምስክር መሆን እችላለሁ ምክንያቱም በጣም አስቸጋሪ በነበሩ ቀናቶቼ በማመንና የእግዚብሔርን ቃል በህይዎቴ ላይ በመናገር ሞክሬ አይቻቸዋለሁ፡፡

የእግዚብሔርን ቃል ድምፃቸንን ከፍ አድርገን ስንናገር የሚፈጠር ኃይል አለ፡፡ የእግዚያብሔርን ቃል በአስቸጋሪ ሁኔታዎቻችን ወቅት ስንናገረውና በተለይም ደግሞ ስናሰላስለው በህወታችን የሚፈጠር ነገር አለ፡፡

ቃሉን ማንበብና ቃሉን ማሰላሰል በጣም ታላቅ ተግባር ነው፡፡ ነገርግን ድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ ስታውጁት ደግሞ ከእግዚያብሔር ከራሱ ጋር ትገናኛላችሁ፡፡እግዚያብሔርም ኃይሉን በእናንተ ህይዎት ላይ ይለቀዋል፡፡

የእግዚብሔርን ቃል እንድታነቡና እንድታሰላሰሉ አዕመሯችሁንም ከእርሱ ጋር እንድታቆራኙ ደግሞም ድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ እንድትናገሩት አበረታታችኋለሁ፡፡ ህይወታችሁን ለመቀየር አዕምሯችሁን በዚህ መልኩ መቃኘትና የእግዚያብሔርን ቃል ድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ ማሰማት አለባችሁ፡፡የእግዚብሔርን ቃል ድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ አሁን ላላችሁበት ሁኔታ ተናገሩ፡፡


ጸሎት ማስጀመሪያ

እግዚያብሔር ሆይ የቃልህን ሙሉ ኃይል በውስጤ እንዲሰራ እፈልጋለሁ፡፡ ከማንበብ ጎን ለጎን ቃልህን ማሰብ እሻለሁ ዛሬ በህይወቴ ላይ መናገር እሻለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon