ከልብ መታዘዝ

ከልብ መታዘዝ

አምላክህ እግዚአብሔር ይህን ሥርዓትና ፍርድ ታደርግ ዘንድ ዛሬ አዝዞሃል፣ አንተም፣ በፍጹም ልብህና በፍጹም ነፍስህ ጠብቀው አድርገውም፡፡ ዘዳ 26 16

ከእግዚአብሔር ጋር ያለን የልብ ወዳጅነት የሚረጋገጠው አንደኛውና ዋነኛው መንገድ ለእርሱ የመታዘዝ ልብ ሲኖረን ነው፡፡ ልባችን ንፁህ ሲሆን የእርሱን ምሪት በጣም እንወዳለን የታዛዥነት ፍላጎታችን በጣም ይጨምራል፡፡ የእርሱን ድምፅ ለመስማት በተጠንቀቅ በመቆምና ወዳጅነታችን የጠነከረ ይሆናል፡፡ ለድምጹም ቅርብ እንሆናለን እግዚአብሔር በዚህ ምድር ላይ እያለን ከቶውኑ ወደ ፍጹምነት እንደማንመጣ ያውቃል፡፡ ነገር ግን ፍጹም ልብ ለእርሱ ሊኖረን ይገባል እርሱን የምፈልግና የምወድ እርሱን ደስ የሚያሰኝና የእርሱን ክብር በምሥጋና የሚያወጣ ልብ ሊኖረን ይገባል፡፡

ከእግዚአብሔር ጋር ባለህ ኅብረት ባለክ መጠን ኅብረትህ የሚመሠረተው በእርሱ ማንነት ላይ እንጂ እርሱ ለአንተ በሚያደርገው ነገር ላይ የተመሠረተ መሆን እንደሌለበት ፈጽሞ መርሣት የለብህም፡፡ የእርሱን መገኘት በመፈለግ ላይ ልትመሠረት ይገባሃል እንጂ እርሱ በሚያቀርብልህ ነገሮች ላይ አይሁን ፊቱን እንጂ እጁን አይደለም፡፡ እንዲህ ከሆነ ከእርሱ ጋር ላለህ ኅብረት ልከልልህ ምክንያት ይሆንብሃል፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ኅብረት ጥንካሬው የሚለካው እራሳችን ከእርሱ ጋር ያለን ኅብረት ላይ በማተኮር እንጂ እንደጓደናችን በመቁጠር አይደለም፡፡ እንደ ሰው ልጅ ጓደኛ ሊሆኑልን የፈለጉትን ሰዎች በማግኘት አይደለም የምንደሰተው ምክንያቱም ምን ነገር ሊጠቀሙ ፈልገው እንደተወዳጁን የማወቅ ችሎታ ስላለን ነገር ግን ለንፁህ ልብና አስተሳሰብ ያላቸው ሰዎች ግን እንዲሁ በእኛ ደስ ስለሚላቸው ሊቀርቡንና ጓደኛና ወዳጅ ሊሆኑን የፈለጉትን ስናገኝ ደስ ይለናል፡፡ ይሄ የሕይወት መመሪያ ደግሞ ከእግዚብሔር ጋር ባለን ሕብረትም ይሰራል፡፡


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- ከእግዚአብሔር ጋር ያለ ኅብረትና ግንኙነትህ በእርሱ ማንነት ላይ እንጂ እርሱ ለአንተ በሚያደርግልህ ላይ አይሁን፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon